ሰካራም ሰው ያገባች ሴት ሙሉ በሙሉ ተበድላልቸ ማለት አይቻልም ። ከስካሩ የሚመጣ ነፃነትን ታገኝ ይሆናል ።
ጥንብዝ ብሎ ሰክሮ እየተንገዳገደ መሳቂያ መሳለቂያ ቢያደርጋትም ፥ በየቀኑ ሰክሮ ወደ ቤቱ የሚገባ ወንድ ፥ ለሰነፍ
ሴት እንደ እረፍት ነው ። ሰካራም ወንድ በሚዞር ምድር ላይ ቆሞ ፥ ቤቱ ይፅዳ አይፅዳ ሊያስተውል አይችልም ፥
ልጆቹ በግዜ ይተኙ አይተኙ የሚያውቀው ነገር የለውም ፥ በቤቱ ውስጥ ምን እየተከናወነ እንዳለ የሚያውቅበት አንዳች
የጊዜ አጋጣሚ የለውም ።
የሰካራም ትዳር ጥሩ ጎኑ ፥ ጥፋቱ የአደባባይ ምስጢር መሆኑ ነው ። አላደረኩትም ፥ አልፈፀምኩትም ፥ አልወደቅሁም ብለህ መካድ እንዳትችል ፥ ገበናህ እንደ እብድ ጎጆ አፉን ከፍቶ ኡኡ ይላል ፥ ጓዳህ በጨበጥከው መለኪያ ላይ ይጮኻል ፥ ስለዚህ ለሽማግሎችም ፥ ለፍርድም ፥ ለትዝብትም የቀለለ ነው ። በመቅለሉ የቀለለ ነገር ምን ያህል ጥቅም እንዳለው ባልረዳም !
የወያኔ መንግስትን ጉድ እና ጉዳይ ሳጤነው ፥ ኢትዮጵያ ሰካራም ባገባች እናት ትመሰልብኛለች ። ሃላፊነት የመይሰማው ፥ ልጆቼ ምን ሆኑ ብሎ የማይጨነቅ መንግስት ። የህዝብ ሃብትን የግል ደስታን እና ምኞትን ለማሳካት እና ለማሳደድ ያለ አንዳች ሃፍረት የሚጠቀም መንግስት ፥ በየጎዳናው ሃጥያት የሚሰራ መንግስት ፥ ደግሞ ደጋግሞ የወደቀ ፥ ግን እየተንገደገደም ቢሆን ቆሜያለሁ ብሎ ሊያወራ የሚሻ መንግስት ፥ ስካሩን እንደ ቅዳሴ አሳምሮ ሊያስርፅብን የሚዳዳው መፃጉ ፥ በንፁሃን ደም ሰክሮም ፥ ለጎረቤቶቹ « እኔ » እያለ የሚያወራ ሃፍረተ ቢስ መንግስት ፥ ከስካሩ ባሻገር ፥ ቤቱ ተኮራምቶ ቁጭ ያለን ህዝብ « የት ሂደህ ነበር » እያለ እንደ ፋንቱ ማንዶዬ የሚሞግት እንከፍ አምባ ገነን መንግስት ሰካራም መንግስት ነው ። ሰካራም ስርዓት ፥ ንፅህናውን በድብቅ ቢያውጅም በጠራራ ለወደቀበት እና ላፈሰሰው ደም ፥ ምስክሩ ሚስቱ ብቻ ሳትሆን ህዝብም ጭምር ነው ! ጩኸቱ የስካሩ እንጂ የምክንያቱ እንዳልሆነ በውሎው እና በማንነቱ ፥ በግብሩ እና በታሪኩ ልንረዳ እንችላለን !
በሰካራም መሪ ስር ያለ ህዝብ ያለመታደሉ ያለመታገሉ ውጤት ነው ። ማንም ከሰካራም ጋ ባንድ ጣራ ስር የመኖር ግዴታ የለበትም ! እንዲህ ያለው አባወራ ፥ የውደቅት ውራ ነውና ሰማኒያችንን መቅደድ አለብን ! አይሆንም በቃኸኝ ማለት አለብን ! መፋታት አለብን ! አይመጥነንምና!

No comments:
Post a Comment