Friday, August 5, 2016

ኢትዮጵያ ሃገርህ አይደለችም !



ኢትዮጵያ ሃገርህ አይደለችም ! ሃገርህ ያልሆነችው ደሞ አንተ ፈቅደህ ስለሰጣኸቸው እንጂ እነሱ ደፍረው ስለቀሙህ ብቻ አይደለም ። ዛሬ ሃዋሳ ያንተ አይደለም ። ሃዋሳ የትግሬ ወያኔ ነው ። ሃዋሳ የትግሬ ወያኔ የሆነው የትግሬ ወያኔ ከጋሞው ፥ ከሽናሻው ፥ ከኩሉ ኮንታው ፥ ከዶርዜው የተሻለ ስለሆነ ሳይሆን በዝምታ ሃገሩን የሚቀማ ህዝብ ስላገኘ ነው ።

ሃገርህ ያንተ አይደልችም ስንል በስራህ የምትከበር ፥ በምግባርህ የምትመሰገን ሳይሆን በማንነትህ የምትረገጥ እና በማንነቱ የሚረግጥህ ስላለ ነው ። አንተ ትግሬ ካልሆንክ ከነ መለዮህ ትረገጣለህ ። ትግሬ ካልሆንክ ስራህን ካንተ በታች ባለ ሰው ትዕዛዝ ትለቃለህ ፥ ትግሬ ካልሆንክ የምታደርገው ነገር በሙሉ ክትትል ይበዛበታል ፥ ትግሬ ካልሆንክ አረማማድህ ፥ አቋቋምህ ፥ አለባበስህ ፥ እምነትህ ሁሉ ፖለቲካ ነው ። እንደ ሰው ለመኖር በማትችልበት ሃገር እንደ ዜጋ መኖር እንዴት ትችላለህ ? ያንተ ብቸኛ መብት « የመገዛት መብትህ ብቻ ነው »። በትምህርት ከሌሎች ስለተሻልክ ፥ ወይም በአስተሳሰብ እና በግብር ስለላቅህ ሳይሆን በደምህ ነው ስራ የምትሰራው ። የሚከፈለህ ለደምህ ነው ። እድገት የሚሰጠው ለደምህ ነው ። ሹመት የሚነፈግህ በደምህ ምክንያት ነው ። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ወረፋ የሚይዘውም ሆነ ጉዳይ የሚያስፈፅመው አሰሪና ሰራተኛ ፥ ባለጉዳይ እና ጉዳይ አስፈፃሚ ሳይሆን ደም ነው ። ደምህ ከወርቅ ደም ወገኖች ካልሆነ ፥ ደምህ ከሩቅ ሌሎችን እያየ የሚቀና እንዲሆን ተወስኖበታል ማለት ነው ።


ልጆችህ ትግሬ ካልሆኑ ፥ ቢማሩ እጣ ፈንታቸው ስደት ነው ፥ ስደት እምቢ ብለው ቢኖሩ ደሞ እስር። ትግሬ ካልሆንክ በአስተሳሰብም ሆነ በአመለካከት ነፃ መሆን አይፈቀድልህም ። በሙያ ሃኪም ልትሆን ትችላለህ ፥ ክሊኒክ ከፍተህ ስራ ለመስራት ፍቃድ አግኝተህ ስራ መጀመር ትችል ይሆናል ፥ ስራህን ባግባቡ ስትሰራና ከነሱ ጋ ተፎካካሪ መሆን ስትጀምር ግን ሃኪምነትህ እና እያበረከትክ ያለኸው አስተዋፆ ሳይሆን ማንነትህ ነው የሚታየው ። አማራ ወይም ኦሮሞ ሆኖ በሽተኛ ቢያድን እና ትግሬ ሆኖ በሽተኛ ቢገል እንደጥፋተኛ የሚቆጠረው ያዳነው እንጂ የገደለው አይደለም ።

ትግሬ ከሆንክ ፥ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ገብተህ ገና ሳትመረቅ ስራ ተዘጋጅቶ ይጠብቅሃል ፥ ትግሬ ካልሆንክ ግን ተመርቀህ በስራ ፍለጋ መንከራተት ሰልችቶህ እንዴት ከአገር መውጣት እንዳለብህ ማሰብ እጣ ፈንታህ ይሆናል ። ትግሬ ሆኖ መሬት መግዛትም ሆነ ፎቅ መስራት ፥ ከባንክ ብር መበደርም ሆነ አስመጪና ላኪ መሆን የሚገርም ነገር አይደለም ። ደምህ በቀጥታ ለእንደዚህ ያሉ ጉዳዮች ብቁ ያደርግሃል ። ትግሬ ሳትሆን ከተሳካለህ ፥ የሚሳካልህ እስኪመቱህ ድረስ ብቻ ነው ። እስኪቀሙህ ብቻ ነው ። እስኪያስሩህ እና እስኪፈርጁህ ብቻ ነው ።

በኢንቨስትመንት ስም ወደ ሀገራቸው ከገቡት ውስጥ እነማን ናቸው የተሳካላቸው ? እነማንስ እንደ እብድ ብቻቸውን እያወሩ ነው ? እነማንስ በገቡ አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሃገሩን ለቀው ተመልሰው ወጥተዋል ? እነማን የነማንን ንድፈ ሃሳብ ቀምተው ፥ የኔ ብለው በተሰረቀ ፕሮጀክት በልፅገዋል ?!

አማራ ወይም ኦሮሞ ወይም ጉራጌ ወይም ሌላ ከሆንክ መሬት ቢሰጥህም ሆነ ቢፈቀድልህ ባንድ ሌሊት እስር ቤት ልትወረወር ትችላለህ ፥ ሊተፋብህ ይችላል ፥ ልትዋረድ እና ልትሰደብ ትችላለህ ። ይሄን የሚያደርገው የቀጠርከው ዘበኛህ ሊሆን ይችላል ። ትግሬ ከሆነ እንዴት አይችልም ። ባለ ወርቅ ደም ነዋ!

እስኪ ትናንት የግል ዩኒቨርስቲዎችን አቋቁመው ትውልድ ከጠቀሙት ትግሬ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያኖች ውስጥ አብዛኛዎቹ ዛሬ የት ናቸው ? የስኳር ፕሮጀክት ጀምረው ገና ቀና ሲሉ ወገባቸውን ተመትተው ፥ ተራቁተው ፥ ተሰድበው እና ተዋርደው ባዶዋቸውን የተሰደዱት ትግሬ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያኖች ምን እያሉ ነው ? ሃያት መኖሪያ ቤትን የመሰረተው አያሌው ፥ እነ ኤርሚያስ አመልጋ፥ የዱጉማ ሁንዴ ቤተሰቦች ፥ እነ አከሌ እነ አከሌ ዛሬ የት ናቸው ? ለምን የሆኑትን ሆኑ ? ለምንስ ይኽ ሁሉ መከራ ገጠማቸው ? ባለ ወርቅ ደም አይደሉማ! የተፈጠሩበት ማንነት የሚያስቀጣ ነዋ! በሃገራቸው እንደሰው ተከብሮ ለመኖር የሚመጥን ማንነት የላቸውማ!

ዛሬ ሚኒቴሪ ተራ ጉራጊኛ በዲዲቲ የጠፋ እስኪመስል ፥ ያን ታታሪ ህዝብ አዋክበው ፥ አዋርደው ፥ አሳደው እነማን ናቸው ቦታውን የያዙት (የሞሉት ?) የቀሚዎቹ ማንነት ከማንስ የተደበቀ ነው ?
ሀጎስ ከየት አባቱ ባመረተው ቅቤ ነው የቅቤ በረንዳውን የያዘው ? ከየት አባቱ ! ሃጎስ ማን ስለሆነ ነው ብቻውን በሀገራችን አዛዥ የሆነው ። ካንተ ስለሚበልጥ ወይም ስለሚሻል ሳይሆን ሃጎስ ባለ ወርቅ ደም ስለሆነ ። ታዲያ እንዴት ከሀጎስ ጋ እንዲህ እየተረገጥክ አብሮ መኖር ፈለግህ?

ሰማህ ባለ ወርቅ ደም ካልሆንክ ከነ መለዮህ በወርቅ ደም ጫማ ትረገጣለህ !
ይህንን ለማቆም ተነስ ! ሃገርህ ነው ! መብትህ ነው ! በናትህ ይቆጭህ እንጂ !

ሄኖክ የሺጥላ

No comments:

Post a Comment

የምጣዱ እያለ የእንቅቡን፤ የእርስ በርስ ግጭት እና የመንግስት ምላሽ

በያሬድ ሃይለማሪያም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም ግጭቶች መበራከታቸው እና መፈናቀል መቀጠሉ የአገራችንን ፖለቲካ አሳሳቢ እያደረገው እና አገሪቱንም ወደ ችግር ውስጥ እየከተታት ይመስላል። መንግስት ለችግሮቹ የሚሰ...