Thursday, July 28, 2016



የምንፅፈው የኛን የ ልብ ወለድ ታሪክ ብቻ ከሆነ ፥ የበሬ ወለደ ሃሜት ከሆነ በእርግጥ ወያኔ መስጋት ያለበት አይመስለኝም ። የኢትዮጵያዊያን ስቃይ በገሃዱ አለም የሌለ ፥ አንድ ከባህር ማዶ ቁጭ ብሎ ፥ ቁጭ-በሉ ተረት የሚተርክ ልጅ የሚተርከው ታሪክ እንጂ ያልነበረ ፥ ያልሆነ እና የማይሆን ፥ የፈጠራ እና የስራ ፈት ስራ ከሆነ ፥ እርግጥ ወያኔ እና ደጋፊዎቹ ( የትግራይ ህዝቦች ) ያን ያህል ሊጨነቁ አይገባም ። ወያኔ የኦሮሞ ልጆችን በጥይት ገድሏል ስንል ፥ አፈታሪክ ከሆነ ፥ ጋምቤላዎችን መሬታቸውን ነጥቋል ብለን ስንል የምድጃ ዳር ወግ ከተባለ ፥ የአማራ ልጆችን በዘራቸውም ምክንያት የዘር ማጥፋት ፈፅሟል ስንል ተራ አሉባልታ እንጂ ያልተፈጠረ እና ያልሆነ ከሆነ ፥ በእርግጥ ወያኔ እና ደጋፊዎቹ ሊጨነቁ አይገባም ።

ወጣቱ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመርቆ ስራ አጥ ሆኖ በየከተማው ይንከላወሳል ስንል ያልነው ያልሆነ እና ያልተደረገ ከሆነ ፥ ባንፃሩ ደሞ ደናቁርት እና ቦሃዎች የሃገሪቱን ዋና ዋና ቦታዎች በዘራቸው ተመርጠው ተቆጣጥረው ፥ ተንቀባረው ይኖራሉ ስንል ሃሜት ከመሰለ ፥ በአየር መንገድ ውስጥ ከተቀጠሩት ተቀጣሪዎች ከ ሰማኒያ አምስት በመቶ በላይ የትግራይ ተወላጅቾ ናቸው ስንል ውሸት ከሆነ ፥ የመከላከያን ከሚቆጣጠሩት ጀነራሎች ውስጥ 98 ከመቶ በላይ ትግሬ ናቸው ስንል ፍሬ ከርስኪ አልባልታ እንጂ በእውነት ላይ የተመሰረተ አይደለም ከተባለ እና መረጃውም ካለ ፥ በአዲስ አበባ ፥ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ፥ በአማራ ክልል ፥ በደቡብ ፥ በአፋር እና ወዘተ የፎቁ ፥ የመሬቱ ፥ የኢንዱስትሪው ፥ የማዕድን ማውጫው ፥ የጥጥ ማምረቻው ፥ የሰሊጥ እና የኑግ እርሻው ፥ የአበባ ችግኝ ማፊያው የትግሬ ነው ፥ ለትግሬ ነው ፥ በትግሬ ነው ስንል ያልነው ሁሉ ምንም መሰረት የሌለው የጥላቻ ወሬ ከሆነ ፥ በእርግጥ ወያኔም ሆነ ትግሬዎች ሊያሳስባቸው አይገባም ። ሊያሳስባቸው የሚገባው የምንለው ሁሉ እውነት የሆነ እንደሁ ብቻ ነው !


ሄኖክ የሺጥላ

No comments:

Post a Comment

የምጣዱ እያለ የእንቅቡን፤ የእርስ በርስ ግጭት እና የመንግስት ምላሽ

በያሬድ ሃይለማሪያም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም ግጭቶች መበራከታቸው እና መፈናቀል መቀጠሉ የአገራችንን ፖለቲካ አሳሳቢ እያደረገው እና አገሪቱንም ወደ ችግር ውስጥ እየከተታት ይመስላል። መንግስት ለችግሮቹ የሚሰ...