‹‹ሀገር አለኝ ለማለት ነፃ ሀገር የመፍጠር ግዴታ አለብህ!!!››
-------------------------------------------------------------------------------------------------------
ውድ የማህበራዊ ድህረ-ገፅ ተከታታዮቼ ሀገራችን ከምን ጊዜውም በላይ የዜጎቿን እርዳታ ትሻለች፡፡ የኢህአዲግ መራሹ መንግስት በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ ፍፁም አንባገነናዊና መረን የለቀቀ እየሆነ ያለበት ሁኔታ በግልፅ እየታየ ነው፡፡ የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በአንባገነኑ መንግስት ጠብ መንጃ ስር ወድቀዋል፡፡ ፍትህ፤ነፃነት፤እኩልነት፤ገለልተኛነት የሚባል ነገር ኢህአዲግ ሀይሉን አሟጦ በመጠቀም በመስራት ላይ ነው፡፡ የዜጎች ከእለት ወደእለት እየተባባሰ የሚመጣው የኑሮ ብስቁልና ሰሚ አጥቶ በህዝብ ገንዘብ በሚተዳደሩት ሚዲያዎች የአድገናል ተመንድገናል ስላቅ እየተሰለቀበት ነው፡፡ የህዝብ ድምፅ በኢህአዲግ የማስመሰያ ምርጫ እየተዘረፈ ህዝብን የስልጣን ባለቤት የማድረግ ሂደቱ ደም አፋሳሽና የአቀበት ያህን የከበደበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ይህ አልበቃ ብሎ ኢህአዲግ በሀገሪቱ ጠንካራ የሚባል ህዝባዊ መሰረት ያላቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመበታተን፤ለማጥፋት ሰፊ የሆነ አንባገነናዊ መረቡን ዘርግቶ ሌት ተቀን ሳይል በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ እልፍ ለህዝብ ነፃነትና እኩልነት መከበር በሰላማዊ መንገድ የታገሉ ፖለቲከኞች፤ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ኢህአዲግ ለዚህ ተልእኮ ባዘጋጃቸው ቃሊቲና ቂሊንጦን በመሳሰሉ አሰቃቂ እስርቤቶች የግፍ ፅዋ በመጎንጨት ላይ ናቸው፤ገሚሶቹም ሀገር ጥለው ተሰደዋል፡፡ …..በኢትዮጵያውያን ታሪክ ከፍተኛ ሀገራዊ ውርደት የተከናነብንበት ወቅት ቢኖር በኢህአዲግ የአገዛዝ ዘመን ነው፡፡ እንደአንድ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ይህ ሂደት በዚህ ሁኔታ እንዲቀጥል መፍቀድ ክብርና ማንነትን ከመሸጥ፤ አልፎ ለተተኪው ትውልድ የባርነትን ቀንበር አውርሶ ማለፍ ነው፡፡
የኢህአዲግ መንግስትን በሰላማዊ መንገድ ታግሎ ለማስወገድ ሰፊ ህዝባዊ መሰረትዘርግተው ጉንቶ የነፃነት አርበኞችን በመስዋትነት እየገበሩ፤የኢህአዲግን የአፈና መረብ ተቋቁመው ያነገቡትን የለውጥ ጉዞ ዳር ለማድረስ አቅም ካላቸው ፓርቲዎች መካከል አንድነት ፓርቲ ንባር ቀደሙ ነው፡፡ ሆኖም ግን ኢህአዲግ በተለመደው አካሄድ የአንድነትን ህልውና ለማቀጨጭና የህዝብን ተስፋ ለማምከን በምርጫ ቦርድና ጥቂት ሆድ አደር ሰርጎ ገቦች አማካኝነት የከፈተውን ዘመቻ መላው ኢትዮጵያዊ የሚረዳው ሀቅ ነው፡፡ ኢህአዲግ በተለመደው አካሄድ የህዝብ ተስፋ የሆኑ ፓርቲዎችን በማስወገድ ፓርቲነታቸው እንኳ በውል ከማይታወቅ በየስርቻው ከተደቀሉ ፀረ-ህዝብ ፓርቲዎች ጋር በመሆን የይስሙላ የምርጫ ድግስ እያዘጋጀ ታጅቦ ቤተመንግሰት የመግባት መርሀ ግብሩን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በመሆኑም ይህን የኢህአዲግ የተለመደ አካሄድ በቃህ የምንልበትና ታሪካዊ ገድል የምንፅፍበት፤ታሪካዊ አጋጣሚ በአንድነት የለውጥ ተጓዦች ተጀምሯል፡፡ በመሆኑም መላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ልዩነታችንን በማቻቻልና አትኩሮቶቻችንን በለውጥ ላይ በማድረግ በአንድነት ፓርቲ ላይ የተከፈተውን ዘመቻ የለውጥ ችቦ መለኮሻ ግብአት በማድረግ ሀገርንና ትውልድን የማዳን ሀላፊነታችንን እንድንወጣና ፓርቲው በአሁኑ ሰዓት ከኢህአዲግና ከተላላኪዎቹ ጋር አንገት ለአንገት ተናንቆ እያደረገ ያለውን ትግል በመደገፍ ብሎም ቀጣይ ለሚወስናቸው ፖለቲካዊ ውሳኔዎችና ጥሪዎች ሁሉ አጋርነታችሁን እንድታሳዩ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡ …….ድል የህዝብ ነው!!!

No comments:
Post a Comment