Sunday, May 24, 2015

ዊ አር ኦን ዘ ራይት ትራክ

ጠንጋራው ሃይለማርያም ደሳለኝ ። ያንን ሸውራራ አይናቸውን እያቁለጨለጩ ከአልጀዚራ ወኪል ጋ ያደረጉትን የምርጫ ሰሞን ቃለ መጠይቅ ሰማሁ ። ለሁሉም ነገር ሐዝን ( has'ን ) ብቻ መጠቀም የሚወዱት እኝህ ጠይም አሳማ ፣ ለተለያዩ ጥያቄዎች የሰጧቸውን መልስ ሳደምጥ የተሰማኝን ለማካፈል ይህንን ጻፍኩ ። አዲስ መስመር

ጋዜጠኛዋ ስለተለያዩ አለማቀፋዊ ድርጀቶች እና እነሱ ስለሚያቀርቡባቸው ትችቶች ትጠይቃለች ። ሞ ኢብራሂም ስትላቸው ፣ ።አይ እሱን አውቀዋለሁ ፣ ሱዳናዊ ነው ፣ ጏደኛዬ ነው " ብለው ይመልሳሉ ። ወይኔ እኔ ብሆን ጠያቂው "ታዲያ ጏደኛዎ ሲወቅሶ ፣ ጏደኛዋ በሰብአዊ መብት ጥሰት ሲከሶ ምን ተሰማዎ ?" አረ አይመልሱልኝ አልፈልግም ። "ምን እንደሚሉኝ ስለማውቅ አይንገሩኝ !" ነበር ያለው ያ ልጅ ።


ትንሽ ወረድ ይሉና በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ ነን ያለነው (we are on the right track ) ሲሉ ሰማሁ ። አይ ጠንጋራ መሆን! እርሶ እኮ በቡድንም በግልም ነው የተጠናገሩት ። በመጀመሪያ right ( በትትክክለኛ ) ማለት ምን ማለት ነው ? ሲቀጥል አቅጣጫ / መንገድ ( track ) ራሱ ምንድን ነው ? አረ እየሱስ ይገስጾት !

ስለ ዞን 9 ጦማርያን ይጠየቃሉ ። መለሱ "አሸባሪ ስለሆኑ ነው የታሰሩት !" ምን መረጃ አሎት? ተቆጡ ። ከወንበሩ ነው መሰል ። ስል ዓለም ሁኔታ ሲናገሩ ዛሬ ከነገ ጋ አንድ አይደለም አሉ "( today is not the same as tomorrow )" ፣ እንዴት ነው ግስና ሁኔታ ይስማማልን እንጂ ። የወደፊት ሁኔታን እና መቼትን የመግለጫ ግሶች አሉ እኮ ። እንደነ ( will እና shall ) ያሉ ። ወይስ እርሶ ራሶ እግዚያብሄር ሆኑ ? በዘመናዊ ፊዚክስ ( Modern Physics, particularly in wave analysis and quantum mechanics ) ትምህርት ውስጥ ስሙ ደጋግሞ የሚነሳ ሰው አለ ፣ ኃይዘንስበርግ ይባላል ። ምን አለ መሰሎት ( uncertainty principle በተባለው የቁሳዊ የብርሃን በሃሪ ውይይት ውስጥ : እርግጠኛ ያለመሆን ሕግ ብለው ደስ ይለኛል ) "It is impossible to measure both the position and the momentum of a particle at the same time " ልተርጉምሎት ? በአማርኛ ወይስ በእንግሊዘኛ? እስኪ መጀመሪያ በእንግሊዘኛ "it is impossible to predict the future because we have insufficient knowledge about the present " ""። ስለ ነገ ለመናገር የዘሬ እውቀታችን እምብዛም ነው ስለዚህ አፎትን ይዝጉ ማለት ነው ። ከዛ በተጨማሪ ምንድን ነው እንዲህ ተነስቶ በትንሹም በትልቁም ግስላ መሆን ? ሳስበው እንደው ቢያንስ አንድ ቀንም ቢሆን ተቆጥቼ ልውጣ ያሉ ይመስላሉ ። ሁኔታዋ ግን ሳይቆነጠጡ እንዳደጉ ያሳብቅቦታል ።

ቀጠሉ ። ድህነትን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ቢያንስ 10 ወይም 15 ዓመት እንፈልጋለን ። እንዴ ሀይልዬ በ 10 እና አስራምስት አመትማ ድህነት ራሱ ከኢትዮጵያ ጠፍቶ ይወጣል ። በቃ አልፈልጋችሁም ይላል ! ቢያንስ ድህነቱን ራሱ አክብረው የሚይዙት ሰዎች ሳይፈልግ ይቀራል ብለው ነው ? ለነገሩ ጌታዎም "የዛሬ 20 ዓመት የኢትዮጵያ ሕዝብ በቀን ሶሥቴ ይበላል ብለውን ነበር" ። የማይደርስ መስሏቸው ። እሳቸው ይኸው 24 ሰዓት አፈር እየበሉ ነው ። ይገባቸዋል !

አሁንም ቀጠሉ ። እርሶ የመወሰን ኃይል የሎትም ( ቴዲ ቢር ኖት ) ( you are a teddy bear ) ስትላቸው ፣ "ተሳስተሻል !" አሏት አሁንም እንደተቆጡ ። እኔ ቴዲ ቢር አይደለሁም ። "ከቴዲ አፍሮ ጋ ልታገናኝኝ አስበሽ ከሆነ ተሳስተሻል!" አሉ ( " በዚህ ሆድ አደር በሆዳቸው " ) ፣ እኔም ድርጅቴም ቴዲ ቢር ሳንሆን በጎች ነን ለዚያም ነው በኮሌክቲቭ ( በጥቅል ) ውሳኔየምንተዳደረው ። ወንበሩ ነው መሰል ራሳቸውን ከሟች ጋ አነጻጸሩ ። እሳቸውም ቢሆኑ በራሳቸው አንድም ነገር አድርገው አያውቅም አሉ ። ሰው ስለሞተ ስራው ይረሳል ብሎ የነገሮት ማን ነው ።

ለማንኛውም ምርጫውም ያልፋል ፣ የእርሶም ጊዜያዊ ስልጣን ያልፋል ፣ ትቢቶትም ያርፋል ፣ ልክ እንደ አጎቶት ። ሕዝብ ግን ያሸንፋል ። እርሶ ግን እድለኛ ከሆኑ ዶማ ይሰጦትና ቤተመንግስት ከመግባቶ በፊት ጀምረው ነቅለው ያልጨረሱትን ጉቶ አንድ ይሉታል ።

ይህ ይሉኝታ ቢስ ጽሑፍ ነው ። ለይሉኝታ ቢስ መሪዎች ! በልካችሁ የተሰፋ !




ሄኖክ የሺጥላ

No comments:

Post a Comment

የምጣዱ እያለ የእንቅቡን፤ የእርስ በርስ ግጭት እና የመንግስት ምላሽ

በያሬድ ሃይለማሪያም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም ግጭቶች መበራከታቸው እና መፈናቀል መቀጠሉ የአገራችንን ፖለቲካ አሳሳቢ እያደረገው እና አገሪቱንም ወደ ችግር ውስጥ እየከተታት ይመስላል። መንግስት ለችግሮቹ የሚሰ...