#Ethiopia
"ኣሸባሪዋ" ፍርድ ቤት ቀረበች...!
***************************
ወይዘሮ ኣልጋነሽ ገብሩ ከሌሎች 6 የዓረና ኣባላት በመሆን የተከሰሱበት "የሽብር ክስ" ቀጠሮ ዛሬ ሓሙስ 18 / 03 / 2007 ዓ/ም በላዕለዋይ ቤት ፍርዲ ክልል ትግራይ የሚገኘው ኣዳራሽ ቀርበው የዓቃቢ ህግ ምስክሮች ቀርበው ቃላቸው ኣሰምተዋል።
"የሽብር ክሱ" ተቀይሮ ወደ "ትምህርት ቤት፣ ጤና ኣገልግሎት፣ የግብርና ስራዎችና ሌሎች መንግስታዊ ኣገልግሎቶች በእግሪ ሓሪባ ኣገልግሎት እንዳይ ሰጡ ኣድርገዋል " የሚሉ ሁነዋል።
ወይዘሮ ኣልጋነሽ "በሽብር ክስ" ለ3 ወራት ከታሰሩ በሗላ በ15 ሺ ብር ዋስ ከተለቀቁ በሗላ በእግሪ ሓሪባ የእህል ክምር ቃጠሎ በማጋጠሙ "ተጠርጣሪዎች ናቹ" ተብለው ከሌሎች 6 የዓረና ኣባላት መታሰራቸው ይታወቃል።
ኣሁንም "ኣሸባሪዋ" ወይዘሮ ኣልጋነሽ "....ከዓረና ኣባልነትሽ ካልወጣሽ በእስር ቤት ትበሰብሽያለሽ...." እየተባሉ እየተስፈራሩ ይገኛሉ።
ወይዘሮ ኣልጋነሽ " ከኣረና ኣባልነቴ በፍፁም ኣልወጣም፣ ድካማቹ ከንቱ ነው፣ ኣሁን ኣባት የሌላቸው ህፃናት ልጆቼ ቀይመስቀል እንዲቀበለኝ ብቻ ነው እምጠይቀው...!" በማለት ቆራጥ ውሳኔዋ ኣሳውቃለች።
"ኣሸባሪዋ" ወይዘሮ ኣልጋነሽ ከዓረና ኣባልነትዋ ለማውጣት ማስፈራራት፣ ድለላ፣ ልመናና የማጭበርበር ተንኮሎች ቢፈበረኩም ከኣቋሟ ንቅንቅ ልትል ኣልቻለችም።
የነ ወይዘሮ ኣልጋነሽ ቀጠሮ ለ03 /04 / 2007 ዓ/ም ተቀጥሮዋል።
ወይዘሮ ኣልጋነሽ የኢትዮዽያ ጀግና እናቶች ተምሳለት ናት።
ነፃነታችን በእጃችን ነው....!
IT IS SO...!
No comments:
Post a Comment