Friday, November 28, 2014

አቶ አበረ አበራ የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ

‹‹ኢህአዲግ ከወደቀ በሬ አርዳለሁ!!!››
****ጅብ….. ያው ጅብ ነው!!!****
*************************************
እኚህ ግለሰብ በምርጫ 97 ወቅት የቅንጅት አባል ሁነው ሲሳተፉ የነበሩ ስለስልጣን ጥም እንጅ ስለህዝብ ሮሮና ብሶት ቅንጣት ታክል እንኳ ደንታ የሌላቸው ሆዳም ናቸው፡፡ …….. በኢህአዲግ አምላክ ወደ ጅብነት የመቀየር እቅዴ አይሳካም ብለው ያሰቡት ከንቲባ አበረ፤……ለቅንጅቱ አምላክ እንዲህ ሲሉ ተሳሉ፤…….‹‹ኢህአዲግ ከወደቀ በሬ አርድልሀለሁ!!!………ታዲያ!.. ይኸን የተረዳው የኢህአዲግ መንግስት የስልጣን ጥማቸውን ሊያረካላቸው ወሰነ፡፡ ……. በቀጥታም ወደጅብነት ቀየራቸው፡፡ ………በዚህም ላለፉት አመታት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሾሙ፡፡ …..ከንቲባአበረ ለኢህአዲግ አምላክ በድጋሜ ሌላ ስለት ተሳሉ…….‹‹ ኢህአዲግን ሆዴ እስኪሞላ የስልጣን ዘመኑን አርዝምልኝ››………. ብለው ተማፀኑት፡፡ ………..የስልጣን ጥምና የንዋይ አምሮት ህሊና የነሳቸው እኚህ ግለሰብ፤ ………ስልጣኑን ከተቆናጠጡ ጀምረው፤……… የአርሶ አደሩን መሬት ያለህግና መመሪያ በማን አለብኝነት ሲቸበችቡና በኢንቨስትመንት ሰበብ የግል ካዝናቸውን ሲሞሉ ኖሩ፡፡ …..በዚህም ሳይታቀቡ፤…… የከተማ ቦታዎችን ከግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን በሚሊየን በሚቆጠሩ ብሮች በመቸብቸብ ረብጣ ብር አካበቱ፤………….ከልዩ ልዩ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ በጀትም የድርሻቸውን አነሱ፡፡ ……..ከንግዲህ ኢህአዲግ ቢወድቅም ደንታ አልነበራቸውም፡፡……….. ምክንያቱም አዲስ አበባና ባህርዳር ከተማ ላይ ባለዘመናዊ ፎቅ ባለቤት ሆነዋላ!!!.......... ሶስት ተሳቢ መኪና ባለቤት ሆነዋላ!!!......... በካዝናቸው ውስጥ ረብጣ ብሮችን አስቀምጠዋላ!!!.......... ነገር ግን አንድ ነገር ይቀራቸው ነበር፤…….. ወደፊት ለሚመጣው መንግስት ደግሞ መሳል፤………. ‹‹እባክህ አምላኬ፤……በኢህአዲግ መንግስት የድርሻዬን አንስቻለሁና፤……..እባክህን ሌላ ባለተራ አምጣልኝ››…….. ግን ሳይሉ፤……የህዝብ እንባ ቀደማቸው፡፡
*************************************************************************
የህዝብ እንባ ፈሶ አይቀርምና እኚህ እልፍ አርሶ አደር መከራ ይወርድባቸው ዘንድ ለፈጣሪው የነገረባቸው፤………….. ስንቱ ደካማ አዛውንት ለየታቦቱ ያሰረባቸው፤………..ስንቱ ባለጉዳይ የእጅህን ይስጥህ ያላቸው፤………..ነጋዴው፣ ተማሪው፣ የመንግስት ሰራተኛው፣……..ሁሉም በየፊናው አቅም ባይኖረው፤ በፀሎቱ የታገላቸው የቀን ጅብ ከንቲባ አበረ፤……… ‹‹የበይዎች አለመስማማት ለተበይዎች ይበጃል››……. እንደሚባለው ያለማንም ከልካይ የህዝብን ሀብት ሲመዘብሩ ኖረው፤ በቅርቡ በአርሳቸው ስር ሆነው ከሚዘርፉ ሌሎች ጅቦች ጋር አለመግባባት ውስጥ በመግባታቸው፤……….. የሙስና ቅሌታቸው በየአደባባይና በየመድረኩ ተጋልጦ ወጣ፤ የእርሳቸው ብቻ ሳይሆን የሌሎች ምክትል ጅቦች ሆድም አብሮ ተበረበረ፡፡ ………… ምንም እንኳ ኢህአዲግ መብቱን የጠየቀን እንጅ ጅብን ለፍርድ እንደማያቀርብ ቢታወቅም ህዝቡ ግን ከፈጣሪው ምላሹን አገኘ፡፡…………….. በሂደቱ ብሶቱን ባገኘው አጋጣሚ እየገለፀ ያለው ህዝብ ከንቲባውን ጨምሮ ሌሎች በሙስናው የተዘፈቁት የከተማ አስተዳደር አመራሮች (ጅቦች) ለፍርድ እንዲቀርቡ ቢወተውትም እስካሁን ድረስ የተወሰደ እርምጃ አለመኖሩ ህዝቡን ይባስ አስከፍቶታል፡፡…………. ይባስ ብሎ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር የከንቲባው ጉዳይ የሚታየው በዕኛ በኩል ስለሆነ ከንቲባው በፍርድ ቤት እንዳይጠየቁ የተጀመረ የፍርድ ሂደት ካለም እንዲቋረጥ ትእዛዝ በማስተላለፍ ከንቲባው ወደዛው እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡ ………..ፍትህ እየተጨቆነ፤…..እየተዘረፈ፤….. ላለው የኢትዮጵያ ህዝብ!!!!........

No comments:

Post a Comment

የምጣዱ እያለ የእንቅቡን፤ የእርስ በርስ ግጭት እና የመንግስት ምላሽ

በያሬድ ሃይለማሪያም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም ግጭቶች መበራከታቸው እና መፈናቀል መቀጠሉ የአገራችንን ፖለቲካ አሳሳቢ እያደረገው እና አገሪቱንም ወደ ችግር ውስጥ እየከተታት ይመስላል። መንግስት ለችግሮቹ የሚሰ...