የ13 ወር ፀጋዋ ሃገር ዘንድሮን በበርካታ ተፈጥሮና ሰውሰራሽ፣ አጋጣሚና ድርጊያዎች እንዳያልፉት ለማለፍ ከደጅ በመጠባበቅ ላይ ናት።
በበኩሌ የሰማዩ ፈጣሪ ቁጣውን ሹክ ካለበት ደረቅ ዝናምም ሆነ በበርካታ መልኩ የዘንድሮው የ300 ምናምን ቀናት ኑባሬ መልካም ከሚባሉት ሁነቶቹ አስከፊ ገፅታዎቹ በዝተውብኝ ከርመዋል። በጥቂቱ ፪፼፮ እኮ፦
፩. ኢትዮጵያዊያን እህትና ወንድሞቼ በሀገረ አረብ ኢ ሰብኣዊ ድርጊት የተፈፀመባቸው፣
፪. ትንሹ አለምነው መኮንን ትልቁን የአማራ ህዝብ "ለሃጫም" በሚል የሰደበበት፣
፫. የኦሮሞ ተማሪዎች በአደባባይ በጥይት የተቆሉበት፣
፬. አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የፖለቲካ ቁማር የተበሉባት፣
፭. ቴዲ አፍሮ በመርዘኛው ኮካ አድማ ሲፈፀምበት መንግስት በጮቤ የደነሰባት
፮. ሰላማዊ ፖለቲከኞች ታፍነው ቃሊቲ የተመሸጉባት፣
፯. ሙስሊም ኢትዮጵያዊያንና ሰማማዊ ዜጎች በመርካቷችን የዱላ መርግ የተሸከሙባት፣
፰. ጥቂት የነበሩት ነፃ ፕሬሶች ለምልክት ሳይቀሩ መቀመቅ የወረዱባት፣
፱. ጋዜጠኞች በገፍ ሃገር ጥለው የተሰደዱባትና ወዘተርፈ አንኩዋሮቹ ናቸው። እስቲ መልካም የምትሉትን ዘርዝሩልኝ ደግሞ???....... (ኄኖክ ገለታው)
No comments:
Post a Comment