ኩራዝ < ግማሽ በስሎ ግማሽ ሳይበስል የሚወጣ እንጀራ ምን እንደሚባል ታውቂያለሽ?››
አምፖል መልሱን ለመስማት ጓጉታ ‹‹አላውቅም›› አለች
‹‹የመብራት ኃይል እንጀራ›› ይባላል፡፡ አምፖል በሳቅ ስትፈርስ በውስጧ የነበሩት ቀጫጭን ሽቦዎች ረገፉ፡፡ ደነገጠች፡፡
‹‹አንቺ ሳልቃጠል አልቀርም›› አለቻት ኩራዝን፡፡ ‹‹ምን የተቃጠለውም ያልተቃጠለውም አምፖል አንድ ነው፡፡ ሁለታችሁም አትበሩም፡፡ አይዞሽ ማንም አያውቅሽም፡፡ እዚህ ሀገር እንደሆነ የሚሠራው ከማይሠራው ጋር አብሮ ነው የሚኖረው > :: ኩራዝ ቀጠለች ጥያቄዋን ‹ ለምሳሌ መብራት ኃይል ሲባል ሰምተሻል? ኃይል አለ መብራት የለም፡፡ ኔት ወርክ ሲባል ሰምተሻል? ‹ኔት› አለ ‹ወርክ› ግን የለም፡፡ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ሲባል ሰምተሻል? ‹ቴሌ› አለ ‹ኮሙኒኬሽን› ግን የለም፡፡ የሃይማኖት ተቋም ሲባል ሰምተሻል? ‹ሃይማኖት› አለ ‹ተቋም› ግን የለም፡፡ ስፖርት ፌዴሬሽኖችን አልሰማሽም? ‹ስፖርት› የለም ‹ፌዴሬሽን› ግን አለ፡፡ የደንበኛ አገልግሎት ሲባልስ? ‹ደንበኛ› አለ፤ ‹አገልግሎት› ግን የለም፡፡ ነጻ ፕሬስ ሲባልስ? ‹ፕሬስ› አለ ‹ነጻ› ግን የለም፡፡ የርዳታ ድርጅት ሲባልስ? ‹ድርጅት› አለ ‹ርዳታ› ግን የለም፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲባሉስ አልሰማሽም? ‹ፓርቲ› አለ ‹ፖለቲካ› ግን የለም፡፡ ነጻ ገበያስ አታውቂም? ‹ገበያ› አለ ‹ነጻ› ግን የለም፡፡ ዴሞክራሲ ሲባልስ አልሰማሽም? ‹ዴሞ(ሕዝብ)› አለ፣‹ክራሲ(አስተዳደር)› ግን የለም፡፡ በየቢሮው በኮምፒውተር ሲስተም መሥራት ጀምረናል ሲሉ አትሰሚም አዎ ኮምፒውተር በየቢሮው አለ ‹ሲስተም›› ግን የለም፡፡ እንዲህ እያልሽ መቀጠል ነው፡፡››
Hana Boru
No comments:
Post a Comment