Saturday, December 6, 2014

#‎Ethiopia‬ ወያኔ (ኢሕአዴግ) ራሱ ባሰመረው መስመር መጫወት አይችልም

ፓርቲዎች ሕጋዊ ሆነው እንዲቋቋሙ የወጣ ደንብና መመሪያ አለ:: ፓርቲዎች በዚህ በማያፈናፍን የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ለመንቀሳቀስ ጥረት ያደርጋሉ፤ በወያኔ (ኢሕአዴግ) ግን በአማራጭ ፓርቲነት መምጣታቸው በራሱ በጠላትነት ያስፈርጃቸዋል፣ ሚዲያውን ተጠቅሞ የስም ማጥፋት ስራ ማከናወን የየዕለት ተግባሩ ሆኗል፡፡
ሆቴሎች ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና ተገቢውን ግብር ከፍለው የሚንቀሳቀሱ የንግድ ድርጅቶች ናቸው ነገር ግን ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለገቢ ማሰባሰቢያ ያዘጋጁት የእራት ግብዣ በወሮበላ መንግስት ነን ባዮች ዝግጅቱን ሊጀመር ካለበት መጥተው ሰውን መበተንና ወጥ እስከማስደፋት ደርሰዋል፡፡
አንድ የፖለቲካ ፓርቲ የተሻለ አማራጭ እንዳለው ለማሳየት ከሕዝብ ጋር መገናኘት ግድ ይለዋል አለበለዚያ ከሕዝብ የማይገናኝ ፓርቲ በአንድ አላማ የተሰባሰቡ ሰዎች ስብስብ ብቻ ሆኖ ይቀራል፤ ይህ እንዳይሆን ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎቸ በሆቴል ውስጥም ሆነ በመንግስት ተቋማት ውስጥ በሚከራዩ አዳራሾች ዝግጅታቸውን ማከናወን አልቻሉም፤ ሆቴል ቤቶች በደረሳቸው ቀጭን ትዕዛዝ መሰረት ፈቃድ ይጠይቃሉ ስብሰባ ለማድረግ ፈቃድ የማያስፈልገው ቢሆንም ለፈቃድ የሚኬድበት መስሪያ ቤት ሲያሻው የከፈላችሁበትን ደረሰኝ አምጡ ይላል (በጎን ሆቴሎቹን እንዳትቆርጡ እያለ) ሲያሻው ደግሞ ፈቃድ አያስፈልገውም እያለ ይመልሳቸዋል፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሳይያዝ ተይዟል ይላሉ፡፡ የመሰብሰብያ ቦታ በማጣታቸው ምክንያት ከሕዝብ እንዳይገናኙ ተደርገዋል በዚህም ምክንያት በጠባቡ ቢሮአቸው ለመሰብሰብ ተገደዋል፡፡
ከዚህ ቀደም አንድነት ጠርቶት የነበረው ሰልፍ በእገታ ተጠናቋል፤ የዛሬው የሰማያዊ ሰልፍ እገታው በድብደባና እስር ተቋርጧል፡፡ ለዚህ የ24ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ አልቀበልም ብሎ ጠረጴዛቸው ላይ ትተው መምጣታቸውን ከአመራሮቹ ባለፈው ሳምንት ሰምተናል፡፡
ከዚህ ቀደም በ‹‹ልማት›› ምክንያት ለሰላማዊ ሰልፍ ዝግ ነው የተባለው አብዮት(መስቀል) አደባባይ በካድሬነት ለሚያገለግሉት እና የመንገስት የስለላ ክንፍ ለሆኑት የእምነት ተቋማት ሕብረት ሰልፍ ክፍት ሆኖ አይተናል፡፡
ወያኔ (ኢሐአዴግ) ለጻፈው ሕገ-መንግስትም ሆነ ለሚያወጣቸው ሕጎች ደንብና መመሪያዎች ታማኝ አይደለም ለራሱ ላልታመነ አንተ ለምን ታጎበድዳለህ ? እንደሰማያዊ መብትህን ወደ ማስከበር ትሄዳለህ እንጂ፡፡
‪#‎Bravo_Blue‬

No comments:

Post a Comment

የምጣዱ እያለ የእንቅቡን፤ የእርስ በርስ ግጭት እና የመንግስት ምላሽ

በያሬድ ሃይለማሪያም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም ግጭቶች መበራከታቸው እና መፈናቀል መቀጠሉ የአገራችንን ፖለቲካ አሳሳቢ እያደረገው እና አገሪቱንም ወደ ችግር ውስጥ እየከተታት ይመስላል። መንግስት ለችግሮቹ የሚሰ...