ዲግሪማ ነበረን በዓይነት በብዛት
ከቶ አልተቻለም እንጂ ቁንጫን ማጥፋት
ዲግሪማ ነበረን ከእያንዳንዱ ምሁር
አልተቻለም እንጂ
ቅማልን ከሃገር
ዲግሪ ተሸክሞ መስራት ካልተቻለ
አህያስ በአቅሟ ወርቅ ትጫን የለ!!
ዲግሪማ ነበረን - ለወሬ የሚበጅ
ሞያሌን ከሃገር - አልነቀለም እንጂ፡፡
ዲግሪማ ነበረን - በሊቃውንት ተርታ
አላዳነም እንጂ - ከገዳይ በሽታ፡
ዲግሪማ ነበረን - ያገኘነው አምና
አልረዳንም እንጂ - ሊሸኝ ድንቁርና፡፡
አይሸኙበት እንጂ - ዲግሪማ ነበረን
አልመከተም እንጂ - ድህነት ሲያጉላላን፡፡
ጥሮ ተጣጥሮ ዲግሪማ ማግኘት
ለመሆን አልነበር - ለሰው መድሃኒት፡
..
..
ገሞራው (ኃይሉ ገ/ዮሐንስ)
No comments:
Post a Comment