-----መደራጀታችን ለነፃነታችን!!!-------
***********************************************************
አንተ የኢትዮጵያ አብራክ ክፋይ የሆንክ ወጣት ትውልድ ሆይ!!! …..እናት ሀገርህ ትናንት በውጭ ወራሪ ስትደፈር ብሶቷን አላሰማችም ነበር፤ምክንያቱም ያኔ የዛሬዋን ኢትዮጵያን በአደራ ያስረከቡህ ትውልዶች በሀገር የማይደራደሩ፤በፍርሀት ያልተጀቦኑ፤ጀግናና ለሀገር ክብር በአንድነት የቆሙ ፤ ለክብሯ መከፈል ያለበትን መስዋትነት የሚከፍሉ ልጆች ስለነበሯት ነው፡፡ በዚህም እማማ ኢትዮጵያ ለክብሯ ደማቸውን አፍሰው፣አጥንታቸውን ከስክሰው ባለፉት ልጆቿ፤ የአሁኑ ትውልድ እስኪረከባት ድረስ ዳር ድንበሯ ተከብሮ፤ማንነቷ ታፍሮ፤ ቆይታለች፡፡
ዛሬ ግን!....... ኢትዮጵያ!..... ያን ትውልድ ያፈራው ማህፀኗ የነጠፈ ይመስል፤በጥቂት የእናት ጡት ነካሽ ልጆቿ፤ ማንነቷ ተደፍሮ፣አንድነቷ ተከፋፍሎ፤ልጆቿ ተሰደው፤የጠላት አንገት በተደፋበት ምድሯ የአብራኳ ክፋዮች አንገታቸውን ሲደፉ፣ደማቸውን ሲያፈሱ፣እርስ በርስ ሲናከሱ፣…….ለክብር ማንነቷ የሚቆም ልጇን መፈለግ ጀምራለች፡፡ እንዲህም ስትል ትናገራለች ‹‹ አንት ለክብር ማንነቴ ዘብ የቆምክ ወጣት ሆይ!....ዛሬ ለአንተ የኖርኩልህ፤…በአያት ቅድመ አያቶችህ አንድነትና ጀግንነት ነውና፤…..በፍርሀት ቆፈን የተያዙ ልጆቼን አንቃቸው፤ወደህሊናቸውም እንዲመለሱ አድርጋቸው፤ከተከፋፈለ ማንነት ይልቅ ኢትዮጵያዊ አንድነት እንዲፈጥሩም ምከራቸው፤….ያኔ ህብረትና አንድነት ያላቸውን ጠንካራ ሀይል ታየዋለህ፤በኢትዮጵያዊ አንድነት ውስጥ ያለውን ፍቅርም ታጣጥመዋለህ፤…..እናም ልጄ ሆይ!.........በተናጠል መሮጥ ትተህ ከወንድም እህትህ ጋር ተደራጅ ….. ያኔ…..!!! ….. ከዝንጉርጉሩ ማህፀኔ የተገኙት ጡት ነካሾቼ፤ጥቂትና ምንም እንዳልሆኑ ታየዋለህ፡፡ የልጅ ጠላቶቼም፤የወላድ መካን አለመሆኔን ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ ልጄ ሆይ!.....ከአንባገነኖች መዳፍ ታወጣኝ ዘንድ ያልነቃውን አንቅተህ፣የተኛውን ቀስቅሰህ….ለለውጥ…ተደራጅ፣ተደራጅ፣ተደራጅ፣ተደራጅ…….!!!››

No comments:
Post a Comment