ፍሬሾች ነበርን 1998 አ.ም ጂማ .. ወደ ግቢ የገባነው በጣም ዘግይተን ስለነበር ክረምቱን እዛው ቀዩ ጭቃ ውስጥ ማሳለፍ እጣፋንታችን ነበር.. በጣም ያስጠላ ነበር .. የኛ ባች ብቻ ከወ.መ.ሽ (ወጣት መሳይ ሽማግሌ.. ክረምት እየመጡ የሚማሩ ትልልቅ ሰዎች ) ጋር ነበር የምንጋፋው.. አዲስ አመት እየደረሰ ነው ፋይናል አካባቢ .. ማታ ላይ 26 ሰው በሚጭነው ኮሞሮስ ዶርም ውስጥ እኔና ጥቂት ልጆች አለን:: የተቀረው ያው ፈተና ሰሞን እንደመሆኑ ላይብራሪ ወይም ስፔስ ብቻ ትዝ አይለኝም.. አየር ልቀበል ወደ ጓሮ ስሄድ (አየር ልቀበል ልበል እንጂ ) በጣም ጭር ብሏል..
ከጥቂት ቆይታ በኋላ ዶርም ገብቼ እንደተቀመጥኩ .. ኮሪደር ላይ ከፍተኛ የመንጋጋትና የመሯሯጥ ድምጽ መሰማት ጀመረ .. ከዛም ከርቀት ጩሀት, ተኩስ , ሩጫ , የዶርምና የኮሪደር በሮች ሲጋጩ የሚፈጥሩት ሰቅጣጭ ድምጽ ,, ሽብር ሆነ .. ዶርማችንን ግጥም አርገን ዘግተን ቁጭ .ምንድነው ነገሩ? እርስ በርስ እንጠያየቃለን ..ግርግሩ ትንሽ በረድ ሲል ምን ማረግ እንዳለብን ግራ እንደተጋባን ከዶርም ወጣን .. ረብሻ መነሳቱ ግልጽ ነው .. በኋላ ፖሊስ ቢመጣ ዱላው ለሁሉም ሰለሚተርፍ ዶርም መቀመጡ አይመከርም .. ከአንድ አመት በፊት እኛ ሃይ ስኩል ሆነን በምርጫ 97 ግርግር ወቅት ፖሊስ ዶርም እየገባ ተማሪዎች እንደደበደበ ሰምተናል..
ከብሎካችን ስንወጣ ግን ጭራሽ ወደ ውጪ ወውጣት አይታሰብም.. አቅራብያችን ወዳለው ስቱደንት ላውንጅ የሚሮጡ ልጆች ስናይ ተከተልናቸው እዛ ገባን:: የካፌው ሰራተኞች በሩን ዘጉት ትንሽ የሰላም ስሜት ተሰማን .. እናም ምን እንደተፈጠረ እዛው ማጠያየቅ ጀመርን ..
"የዘር ግጭት ነው" ..
"የኦሮሚያ ተማሪዎች እና የትግራይ ተማሪዎች ተጣልተው ነው " ..
"የኦሮምያ ተማሪች .. በኦሮምኛ ያናግሩሃል ካልቻልክ በዱላ" ..
ከወደ ብጥብጡ መሃል ሮጠው የመጡት አየን የሚሉትን ያወራሉ.. እኛም በግርምት እንሰማለን ..ማመን አልቻልኩም.. በዚህ መሃል ድጋሚ ተኩሱ ቀለጠ.. በላውንጁ አንድ መስታወት ግድግዳ በኩል በተምዶ CB ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ደንገዝገዝ ባለው ብርሃን ውስጥ ከርቀት ወለል ብሎ ይታያል .. ሁሉም ወደዛ ሄዶ ተእይንቱን መከታተል ጀመረ.. የሚሮጡ ተማሪዎች.. ከነ ደብተር መጽሃፋቸው የሚወድቁ ተማሪዎች.. የሚያባርሩ ተማሪዎች.. የወደቁትን በዱላ የሚመቱ ተማሪዎች .. አጥር ለመዝለል የሚሞክሩ ተማሪዎች ,, ሴቶች ወንዶች ይጮሃሉ.. ጩኸት ጩኽት ጩኽት! ..
ከዛ ትንሽ ከፍ ብሎ ደሞ .. የሚሮጡ ወታደሮች .. ያገኙትን ተማሪ የሚጨረግዱ ወታደሮች .. የሚተኩሱ ወታደሮች .. ግቢው የጦርነት ቦታ ይመስላል ..
ሰውነቴ መንቀጥቀጥ ጀምሯል.. ምንም ማድረግ ያለመቻል ስሜት .. የሆነ የእልህ እና የንዴት ስሜት.. እንባዬ ሳያስፈቅደኝ መውረድ ጀምሯል ለካ.. ወይኔ #Ethiopia ! ኢትዮጵያ እንዲ ነች?? .. ያቺ በመጽሃፍ ላይ ስለ ታሪ ኳ , እርስ በርስ ተዋድው ስለሚኖሩ ህዝቦቿ , ያነበብኳት ኢትዮጵያ .. ይቺ ነች?? ተባብረው እምቢ ብለው ወራሪ አባረሩ በአንድነት የተባለላት? ... በነጻነት የጥቁሮች ምሳሌ ነበረች ብለው ያስተማሩን? .. መቆም እንኳን አልቻልኩም አፍላ እልሄ ያንቀጠቅጠኛል .. ይቺ ትልቅ ልቤ ደግሞ ያላቅሜ ደም እየረጨች ነው መሰል ሰውነቴ መገታተር ጀመረ .. ዩኒቨርሲቲ እንዲህ ነው?.. እንደነኛ "መሬት ላራሹ" እያሉ ተያይዘው መንግስትን ሲሞግቱ እንደነበሩት .. እንደነዛ ለህዝብ ተሟግተው እንደሚታሰሩት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አይደለንም ማለት ነው?.. እነዛ እንኳን አምና 1997 የስድስት ኪሎ ካምፓስ አጥር ላይ ተደርድረው .. "የህዝብ ድምጽ ይከበር" እያሉ ከፈደራል ፖሊስ ጋር እንደተፋጠጡት ተማሪዎች አይደለንም ማለት ነው?? ..
እኛ እርስ በርስ በጭካኔ የሚደባደቡ ተማሪዎች ነን ማለት ነው??..
ብዙ ጥያቄዎች በሃሳቤ ተመላለሱ...
በዚህ መሃል ያዩኝ ተለቅ የሚሉት የላውንጅ ሰራተኛ መተው እጃቸውን ጣል አርገውብኝ
"ምነው የኔ ልጅ.. ውጪ ነበርክ? ተመተሃል እንዴ?.." አሉኝ ..
"እዚሁ ነበርኩ አልተመታሁም... ደሞም ውጪ ብሆንም አልመታም.. ኦሮምኛ መናገር እችላለሁ መሰለኝ.. የሸዋ ቢሆንም"....
"ምነው ታድያ ? አይዞህ !.." ብለው ሲያቅፉኝ በቃ በደንብ መውረድ ጀመረ እንባዬ .. ጓደኞቼም ወሬ ከሚያዩበት መስኮት ወደኔ መጥተው " ምነው?" አሉኝ.. ሌላ ምንም አላልኩም
"ልቤን ..ልቀመጥ" .. መመታት አለመመታት አይደለም ነገሩ .. ከዚያም በላይ ነው .. እኔ በወቅቱ 18 አመቴ ነው:: የማየውን ክፋት መቀበል አቅቶኝ ነበር .. እውነት አብረው የሚማሩ ኢትዮጵያውያን ወንድማማች ተማሪዎች እንዲህ ተጨካክነው መቀጣቀጣቸውን ማመን አቅቶኝ ነበር:: ... በጣምም ልብ ይሰብር ነበር አጋጣሚው::
ቁጭ እንዳልኩ ጠረጴዛውን በቡጢ ነረትኩት .. ምንም አልተሰማኝም .. በኋላ ግን እጄ ለሆኑ ቀናት ትንሽ ማበጡ ትዝ ይለኛል.. እዛች ቦታ በሃዘን ቁጭ ብዬ በምናቤ የማቃትን ኢትዮጵያ ቀበርኳት .. የለችማ ,, ከአመት በፊት የምርጫ ክርክር ላይ "ሃገሪቷን በዘር በሃይማኖት ከፋፈሏት.. ህዝቡን አጣላችሁት" ..የሚለው የተቃዋሚዎች ክስ ትዝ ይለኛል..
"ፈደራሊዝም የኢትዮጵያ መዳኛ ነው "
የኢሃዴግ መልስም እንደዛው..
በጥንቃቄ ያልተተገበረ ፈደራሊዝም .. ህዝብን ከፋፍሎ በማዳከም የራስን ስልጣን ለማራዘም የተጠነሰሰ ሴራ .. ውጤቱን በአይኖቼ ፊትለፊት አየሁት.. በእኔ እይታ ደብዳቢም ተደብዳቢም ከቋንቋ በስቀር ብዙም ልዩነት የላቸውም.. የመጡት ለመማር ነበር.. ሁለቱም በአብዛኛው ከድሃ በተሰብ የመጡ.. ቤተሰባቸው ተምረው ተመርቀው ስራ ይዘው ኩራት ይሆኑኛል ብሎ የላካቸው.. በሶ, ጭኮ , ዳቦ ቆሎ ,.. ይዘው የመጡ ተማሪዎች .. በአብዛኛው ከ 17-20 አመት እድሜ ያሉ ተማሪዎች .. ከተለያየ የመናገርያ አፍ ይኑራቸው እንጂ ,, የሚያመሳስላቸው ነገር ይበልጣል.. ግን እየተጣሉ ነው.. እየተጠላሉ ነው.. የፖለቲከኞች ሴራና ተንኮል እየተሳካ ነው.. ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊ ወንድሙን እየፈነከተ ነው ,, ኢትዮጵያዊነት እየደማ ነው,,, እያየነው ,,
ረብሻው የተነሳበት ምክንያት ተብለው የሚሰሙት ደግሞ ጭራሽ እርር ድብን የሚያረጉ ነገሮች ናቸው.. እከሌ ዩኒቨርስቲ DSTV ROOM ሁለት ተማሪዎች ይደባደባሉ ያው በማያገባን የአውሮፓ ጨዋታ በኳስ የተነሳ.. ያለ ነው ችግር አልነበረውም .. ችግሩ የተደባደቡት ልጆች የSocial Scienceና የ Education ተማሪዎች ናቸው ማለት ሲቻል.. የManche ደጋፊው ልጅና የChelseaው ደጋፊ ልጅ ተጣሉ ማለት ሲቻል.. የተባለው ግን ሌላ ነው ,, የገባንበት የዘር አዙሪት የጎሰኝነት ሱስ እድሜ ለመሪዎቻችን , ልሂቃኖቻችን ና ለተሳካው ከፋፋይነታቸው .. . ኦሮሞና ትግሬ ተማሪዎች ተጣሉ ተባለ.. ወሬውን በወሬ ስናበዛው ደግሞ ኦሮሞዎችና ትግረዎች ተባለ,, አስቡት አንድ ቀላል የሁለት ጎረምሶች ድብድብ እንዴት መልኩን እንደቀየረ.. ጭራሽ ከእከሌ ካምፓስ እስከ ጂማ .. ከጂማ እስከ እንትና ዩኒቨርስቲ ድረስ ተዛምቶ ,,ስንት ሰው ተጎዳ? ስንት ሰው ሞተ? .. ስንት ሰው ከትምህርት ተባረረ ,, ስንት ቤተሰብ አዘነ ተጎዳ??...
ምርር ያለ የመንግስት ጥላቻ ያደረብኝ ያን ግዜ ነው .. ይሄንን ክፍፍል እንደሚፈልጉት ግልጽ ነው:: ተሳክቶላቸዋል:: እውነት ለመናገር በኛ Batch ታሪክ ተማሪው አንዴ ብቻ ተባብሯል ለሆዱ ሲል ብቻ.. ከዛ ውጪ ሁሌም እርስበርስ ግጭት ነው::
" የ ሃሙስ ሽሮ አብዮት" ትባላለች ያቺ አንድ ግዜ ብቻ የተከሰተች አንድነት .. ሃሙስ ምሳ ሰአት ላይ የምትቀርብ በጣም ዘግናኝ ሽሮ ነበረች ሁሉም የሚጠላት .. እናም አንድ ህሮብ ምሽት አብዮቱ ተጠነሰሰ.. በቦታውም ነበርኩ :: .. ወረቀቶች ተጻፉ..መልእክቱ ባጭሩ
"ሃሙስ ምሳ ሰአት የሚቀርበው ሽሮን በመቃወም .. ሁላችሁም ካፌ ስትሄዱ ምግቡን ተቀብላችሁ እንዳለ ምንም ሳትበሉ የተረፈ ምግብ መድፊያው ላይ እንድትደፉ" የሚል ነው ..ከምሳ ሰአት በፊት የግቢ ፖሊሶች ወረቀቶቹን ከየተለጠፉበት ቢገነጥሉም ሃሙስ ጠዋት ከዶርም የሚወጣው ተማሪ ጽሁፎቹን ስላነበበ , ላልሰማው እየነገረ ዋለ.. ካፌ ምሳ ሰአት የሚገርም ነበር ሁሉም ሰው እየመጣ , እየተቀበለ ሳይበላ መድፋት ጀመረ:: ለካፌ ሰራተኞች ከቁጥጥር ውጪ ሆነ.. ከዛን ቀን በኋላ ያቺ ሽሮ ከጂማ ዩኒቨርስቲ ጠፋች..
የተሳካ አብዮት ነበረ ግን ለምግብ ብቻ ሆኖ ቀረ .. ያቺን ሽሮ እንደጠላናት ዘረኝነትን ብንጠላ .. ያኔ እንደተስማማነው ለሃገር ጉዳይም አብረን ብንቆም.. ብዬ አስባለሁ አንዳንዴ .. ግን አልሆነም .. የሃገራችን እጣ ፋንታ የሆዳችንን ያህል እንኳን አላሳሰበንም:: ከዛን ቀን ጀምሮ ተመርቀን እስክንወጣ ባሉት 4 አመታት.. አንዴ አንዱ ሌላ ግዜ ሌላው ቦታ ቢቀያየሩም .. ሁሌ ሯጩ ተማሪ አሯሯጩ ተማሪ .. እንደሆነ የባከኑ አመታት.. .. ረባሾቹ ምንም ባላረጉ ተማሪ ወንድሞቻቸው ላይ በጭካኔ የሚያሳዩት "ጀግንነት" .. በመጨረሻም ፌደራል ፖሊስ ይመጣ እና ይቆማል .. እነሱም በተራቸው ብቻቸውን ይሮጣሉ .. ድንቄም ጀግንነት !
4 አመታት ! የተለያዩ ረብሻዎች ሲካሄዱ አንዱም እንኳን ተማሪዎች ተባብረው ለአንድ አላማ ቆመው ከመንግስት ወይም ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ጋር የተጋጩበት የለም.. ሁሌ የብሄር .. ሁሌ እርስበርስ .. በጣም ያበሳጫል... አሁንም በየዩኒቨርስቲዎቹ የሚሰማው ከዚህ ታሪክ የተለየ አይደለም.. እንደ ቀድሞዎቹ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተባብሮ መቆም ያለውን ሃይል እና ጥቅም ማንም አልገባውም :: ያሳዝናል .. አምላክ መፍትሄውንና ወዋደድን ፍቅርን ያብዛልን :: ምክንያቱም ከሴረኞች ከሃይለኞች ከሁሉም በላይ ነውና
#ኢትዮጵያ_ለዘላለም_ትኑር
MANDY YONAS

No comments:
Post a Comment