የአንድ ጓደኛችንን እናት ካድሬዎች ሁሌም ይጨቀጭቋቸው ነበር፡፡ አባል ሁኚ ብለው፡፡ እኒህ እናት ብዙ ጊዜ የተለያየ ምክንያት እየፈጠሩ ካድሬዎችን ይርቋቸዋል፡፡ አንድ ቀን ግን ተመሳሳይ ጥያቄ ሲያቀርቡላቸው ‹‹ተውኝ ቤተ ክርስትያን ልሳምበት!›› ብለው እንቅጩን ነገሯቸው፡፡ እኚህ እናት ‹‹ተውኝ ቤተ ክርስቲያን ልሳምበት›› ሲሉ ካድሬነት ክህደት ነው ማለታቸው ነው፡፡ ካድሬነት እምነትን ያስክዳል ማለታቸው ነው፡፡ ካድሬነት ሰብአዊነትን ያስክዳል ማለታቸው ነው፡፡ ካድሬነት እናትነትን ያስክዳል ማለታቸውም ነው፡፡ ከምንም በላይ ግን የኢህአዴግ አባል (ካድሬ) በመሆናቸው ቤተ ክርስቲያን የሚስሙት ሌሎች ባልንጀሮቻቸው እንደሚጠቋቆሙባቸው፣ እንደሚያሙዋቸው፣ እንዲሚርቋቸው ያውቁታል፡፡ ካድሬነት ለእናት አይሆንም!
እናቶች ሩህሩሆች ናቸው፡፡ በመሆኑም ከሚያስር፣ ከሚገድል፣ የ80 አመት አዛውንት እና እርጉዝ ሴት ከሚያስደበድብ ጨካኝ ስርዓት ጎን መቆም ይከብዳቸዋል፡፡ ቢቆሙም በዛ ሴራ ውስጥ አይኖሩበትም፡፡ በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ቢገቡ እንኳ ወጣቶች እንዲታሰሩ፣ እንዲሰለቡ፣ እንዲሰቃዩ ይፈልጋሉ ብሎ ማሰብ ይከብዳል፡፡ ምክንያቱም ልጆች አሏቸው፡፡ እናቶች ናቸው፡፡ ሩህሩሆች!
አሁን ግን እናቶችም እየጨከኑ ነው፡፡ ልጆቻቸውንና የልጅ ልጆቻቸውን ለጨካኞቹ ደህንነቶች አሳልፈው እየሰጡ ነው፡፡ እያሳሰሩና እያስደበደቡ ነው፡፡ እነዚህ በፎቶው ላይ የምታዩዋቸው ‹‹እናቶች›› የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ፊት ለፊት ሱቅ አላቸው፡፡ የኢህአዴግ የሴቶች ሊግ አባላት ናቸው፡፡ እናም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሲገቡና ሲወጡ እያዩ ለደህንነቶች ይደውላሉ፡፡ ደህንነቶች የሚፈልጉት ሰው ሲገባ ወይንም ሲወጣ አሊያም ሌላ የፓርቲው እንቅስቃሱ ሲደረግ ሱቃቸውን ዘግተው በቅርብ ርቀት ወደሚገኙት ደህንነቶች ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡ እነዚህ ‹‹እናቶች›› እነሱ በሚሰጡት መረጃ የልጅ ልጆቻቸው የሚሆኑት ወጣቶች እንደሚደበደቡ፣ እንደሚታሰሩ፣ እንደሚሰቃዩ ጠፍቷቸው አይደለም፡፡ ካድሬነት የእናትነት ርህራሄያቸውን ነጥቋቸው እንጅ ያውቁታል፡፡ ካድሬነት እንዲህ ነው!

No comments:
Post a Comment