#Ethiopia #politics #freedom #change
ብዙ ጊዜ የሚሰማ አንድ የኮካዎች እና የስርዓቱ የዛገ መዝሙር አለ፡፡ በተለይ በማስመሰያዊ የምርጫ ወቅት ጆሮ እስኪያደማ እንደጉድ ይዘፈናል፡፡ "ተቃዋሚዎች አማራጭ የላቸውም፡፡" እኔ መቼስ ለአማራጭ ለአማራጭ ኢህአዲግ ጎን ከተሰበሰቡ ምሁራን ይልቅ በተቃዋሚው ጎን ሊሰበሰቡ የሚችሉ ምሁራን ቁጥር ስፍር እንደሌላቸው በማስረዳት ራሴን አላደክምም፡፡ ቁምነገሩ ራሱ የአማራጭ መኖርና አለመኖር አይደለም፡፡ ለአማራጭ የሚሆን የፖለቲካ ሜዳ እስካሁን አለመኖሩ ነው፡፡
በደርግ ዘመን አማራጭ ስላልነበረ አይደለም ወታደሩ ስልጣኑን የሙጥኝ ያለው፡፡ አሁንም ያው ነው ምሁሩን እያሸማቀቁ እና እያሳደዱ የተረፈውን ከስራ እያባረሩና እያሰሩ ህዝቡን በል አማራጭ የለህም እና ካርድህን ስጠኝ የሚል የሞኝ ሙዚቃ ጆሮ ያደማል፡፡
ሲጀመር መቼ ብሔራዊ መግባባት ተፈጥሮ ነው ስለ ፖሊሲ አማራጭስ የሚወራው? መቼ ህዝብ የስልጣን ባለቤት ሆነና? መቼ ፖለቲካው የኢሊት መሆኑ አብቅቶ ህዝብ ፈራጅ የሚሆንበት ምህዳር ተፈጠረና? መጀመሪያ እንደ አንድ ህዝብ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ተፈጥሯል?? በሰንደቅ ዓላማችን ላይ ተስማምተናል? በፌደራሊዝም አወቃቀራችን ላይ ተስማምተናል? ታሪካችንን ላይ የተቀራረበ አተያይ እንዲኖር ተደርጓል? በጋራ ለመኖር የሚያስችል መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረናል? ስለመሬት ጉዳይ ከህዝብ ጋር ተማክረናል? ይሄ ሁሉ የሀገራችን ውጥንቅጥ መች መስመር ያዘና ነው ስለ አማራጭስ የሚወራው?
ብዙ ርቀት ይቀረናል - ናይጄሪያ እኮ ጆናታን ስልጣን ሲለቅ አማራጭ ተብሎ በቡሃሪ የቀረበው ሙስናን መዋጋት ቦኮሃራም ላይ ጠንካራ እርምጃ መውሰድ ብቻ ነው፡፡ አማራጭ ማለት ብሔራዊ መግባባት ባለው ህዝብ ዘንድ እንዲህ ነው!! እውነት እንነጋገር ከተባለ ዛሬ እኮ ሰማያዊ አማራጭ ከሚላቸው ጉዳዮች በአመዛኙ የፖሊሲ ሳይሆኑ እንደሀገር ልንግባባቸው የሚያስፈልጉ አንኳር ሀገራዊ አጀንዳዎች ናቸው፡፡
የትኛውም ሀገር ላይ 'የፌደራል አወቃቀራችን እንዲህ ይሁን' የሚል አማራጭ የፖሊሲ ተደርጎ ፓርቲዎች ሲከራከሩበት አላየንም፡፡ 'ብሔራዊ ቋንቋ ይኑረን' ተብሎ ፓርቲዎች ሲከራከሩ አልሰማንም - 'መሬት የግል ይሁን የመንግስት' የሚል ንትርክ በፓርቲዎች መካከል የትም ሀገር እንደፓርቲ ፖሊሲ አይቀርብም - በእውነቱ እነዚህ ጉዳዮች ወይ ሪፈረንደም የሚደረግባቸው ናቸው ወይ በስምምነት የሚተገበሩ የአንድ ህዝብ ህልውና የሚረጋገጥባቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች ናቸው! ፡፡
እንበልና → ኢህአዴግ እንደው በምርጫ ከስልጣን ወረዶ ተቃዋሚ ሆነ - ሰማያዊ ለቀጣይ አምስት ዓመት 'አማራጭ' የተባሉ ጉዳዮች ሲያስፈፅም ከርሞ በምርጫ ተመልሶ ቢወርድና መድረክ ወይ ኢህአዲግ ቢመረጡ ለአምስት ዓመት ደግሞ የራሳቸው ፌደራል አወቃቀር የመሬት ጉዳይ ሌላውንም ሲያስተካክሉ - ውሃቅዳ ውሃመልስ - አልተገናኝቶም
እነዚህ ጉዳዮች ናቸው ዛሬም በተቃዎሚች የሚነሱት አማራጮች - እነዚህን ይዘህ ነው እንግዲህ ህዝብን ምረጠኝ እምትለው፡፡ ለኔ ከዚህ በላይ የሀገራችንን ውጥንቅጥና የኢህአዴግን አምባገነንነት አመላካች አይኖርም፡፡ ሀገራዊ መግባባት ሳይኖር መድብለ ፓርቲ ስርዓትም ሆነ ዲሞክራሲ ሊኖር አይችልም፡፡
አይነኬ የሆኑ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ወደ አንድ መምጣት አለብን፡፡ ያኔ ሙስናን አጠፋለሁ፣ ስራ አጥ እቀንሳለሁ፣ ኢኮኖሚውን አረጋጋለሁ . . . በዚና በዛ አድርጌ ስልጣኑ ከያዘው ፓርቲ በተለየ ችግር እፈታለሁ ብለን ፉክክር ማድረገ እንችላለን፡፡ ዲሞክራሲ ማለት ህዝብ እንዲህ ያለ ችግሩን የሚያቀልለት አማራጭ እንዲኖረው የሚያደርግ ስርዓት መገንባት ነው፡፡ አሁን ባለው ነባራዊ ሁናቴ መጀመሪያ መች ስርዓቱን ለሁላችን በሚበጅ መልኩ ገነባነው??? ተጭኖብን እንጂ መቼ ተስማምተንበት ነው ስለ ፖሊሲ አማራጭ ልናወራ የምንችለው?
Be blessed
#Amha

No comments:
Post a Comment