Saturday, April 18, 2015

ደቡብ አፍሪካ ግን አፍርኩልሽ



ከዚህ በፊት፤ ደቡብ አፍሪካ ከአፍሪካ ተስፋ የሚጣልባት ሀገር ናት ብዬ ያሰብኩት ጸጽቶ ሊገድለኝ ነው! በዚህ ዘመን ጎራዴ እየላሱ በጎራዴ የሰውን እድሜ የሚቀጥፉ ሰዎች በዚህ ምድር መኖራቸው ተዓምር ነው። መንግስታቸውስ ቢሆን ደቡብ አፍሪካን የሚያክል ስም ያላት ሃገር እንዲህ አይነት የቀን ጅቦች ሲሰለጥኑባት ምን እያደረገ ነው። ከችግሩ በፊት ችግር ፈጣሪዎች እንዳይበራከቱ ማህበረሰቡን የሚያግዝ ጠንከር ያለ ፖሊሲ... ችግሩ ገፍቶ ሲመጣ ደግሞ ንጹሃን ሰለባ እንዳይሆኑ ጠንከር ፖሊስ ማዘጋጀት ካልቻለ ድሮም ቢሆን በደመነፍሱ ነው የነበረው ማለት ነውኮ! ምናልባትም የደቡብ አፍሪካ ደቡብ አፍሪካነት ከማንዴላ ጋር አፈር ሳይገባ አይቀርም ብለንም እየጠረጠርን ነው!

የኛ ጉዶችስ ምን እያደረጉ ይሆን... ከዚህ በፊት በሳውዲ አረቢያ፣ ከዛ ደግሞ መቼ ለታ በየመን አሁን ደግሞ በደቡብ አፍሪካ ወገኖቻችን ዋነኛ የጥቃት ሰለባ ሲሆኑ ባለስልጣኖቻችን ምን ይሰማቸዋል። ሰዉን ሁሉ ካገር እያባረሩ ለመከራ እና ስቃይ እየዳረጉ ንግስናውስ ለምንድነው። የገዛ ቤተሰቦችን ለማስተዳደር እኮ ባለስልጣን መሆን ሳይሆን አባወራ መሆን በቂ ነው። እና ለከፋ ችግር እያጋለጡ ለክፉ ቀንም የማይደርሱልን ከሆነ ስልጣን ላይ ቁጭ.... ማለታቸው ለራሳቸው ካልቀፈፋቸው ራሳቸው ቀፋፊዎች ናቸው!


የምር በጣም ያበሳጫል። በጣምም ያስጨንቃል። በገዛ ሀገራችን ሳይመቸን በሰው ሀገር ሳይደላን እስከመቼ እንደምንኖር ፈጣሪ ይወቀው!

ለማንኛውም በደቡብ አፍሪካ የምትገኙ ወዳጆቼ አምላክ ከናነተ ጋር ይሁን! ራሳችሁን ጠብቁ! ርስ በርሳችሁም ተጠባበቁ! ፈጣሪም ይጠብቃችሁ! አንድ ቀን ጥርሳችንን ነከስ አድርገን ሀገራችንን ቁማር ከበሉን ሰዎች ባለን ሁሉ ሄደን እስክናስመልስ ድረስ እንግዲህ እርሱ አብሮን ይሁን!!!

ደቡብ አፍሪካ ግን አፍርኩልሽ!!!! ተሸማቀኩልሽ!!!

Abe Tola

No comments:

Post a Comment

የምጣዱ እያለ የእንቅቡን፤ የእርስ በርስ ግጭት እና የመንግስት ምላሽ

በያሬድ ሃይለማሪያም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም ግጭቶች መበራከታቸው እና መፈናቀል መቀጠሉ የአገራችንን ፖለቲካ አሳሳቢ እያደረገው እና አገሪቱንም ወደ ችግር ውስጥ እየከተታት ይመስላል። መንግስት ለችግሮቹ የሚሰ...