Saturday, February 14, 2015

እኔ ግን የምለው ምን እስክንሆን ነው የምንጠብቀው???

አንድን ስርአት ስንቃወም ምክንያታዊ ሆነን ይገባል ባይ ነኝ፡፡ ምናልባት የሚያስተዳደረን መንግስት ዴሞክራሲያዊና የተሻለ አስተዳደር ያለው ሆኖ በኢኮኖሚው ሴክተር ወይም በሌላ ድክመት ካለበት ተፎካካሪ ፓርቲዎች የተሻለ አማራጭ በማቅረብ ሊፎካከሩ ይችላሉ፤ የተሻለ ሀገርም መፍጠር ይቻላል፡፡ በኛ ሀገር ተጨባጭ ሁኔታ ግን ኢህአዲግ እንደሰጠን ስያሜ ‹‹ፍፁም የምንቃወመውና ጠናካራ የሚባል አስተዳደራዊ ጎን (ገፅታ) የሌለው፤ ፍፁም አንባገነናዊ ስርአትን ነው፡፡ ይህን ስል ያለምክንያት አይደለም፡-
- ኢህአዲግ ከመጨውም ጊዜ በላይ ዳር ድንበራችንን ቆራርሶ በመስጠት ታሪካዊዋንና ከነክብሯ የቆየችዋን ኢትዮጵያችን ወደብ አልባና ቅርፅ አልባ አድርጓታል፡፡ ይህም የሚካድ አይደለም፡፡
- የዜጎች የኑሮ ብስቁልና ከአመት አመት እየተባባሰ በመሄድ ህዝባችን ለረሀብና ስደት እየተጋለጠ፤በስደት አለምም ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ታሪካዊ ውርደትን ተከናንበናል፡፡ ይም አይካድም
- የሰብአዊ መብት ጥሰት በሚሰቀጥጥ ሁኔታ የሚጣስባትና ዜጎች ያለምንም ወንጀል የሚታሰሩባት፤ቶርች የሚደረጉባት፤የሚገደሉባት፤….. ቁንጮ አፍሪካዊት አንባገነናዊ ሀገር መሆኗን የአለም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርግቶችንና ተቋማትን ሪፖርት በመመልከት ብቻ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ይህም እየኖርንበት ያለ እውነታ ስለሆነ አይካድም
- የመናገር፤የመፃፍ፤ሀሳብን በነፃ የመግለፅ መብት በአደባባይ የሚጣስባት፤ በዚህም ጋዜጠኞችን በብዛት በማሰር በአለም አራተኛዋ አሳሪ ሀገር ተፈጥራለች፡፡ ይህም አይካድም፡፡
- የብሄር ፖለቲካ የሰፈነባት፤በከፋፍለህ ግዛ መርህ ህዝቦቿ አንድነት እንዳይኖራቸውና አቋማቸውን በአንድነት እንዳያሰሙ በአፈ ሙዝ ቁጥጠር ስር የዋሉባት ይችው ኢትዮጵያችን ናት፡፡ ይህም አይካድም፡፡
- ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በሀገራቸው ላይ የመድብለ ፓርቲ ስርአት ግንባታ አስተዋፅኮ እንዳያደርጉና የተሸለ የፖሊሲ አማራጮች ተጠቃሚ እንዳንሆን፤ …….ገዢው መንግስት ተቃዋሚዎችን ከመደገፍ ይልቅ፤ በማሸማቀቅ፤በመበታተን፤ከአንድ መንግስት የማይጠበቅ ማፊያዊ ተግባር በመፈፀም አማራጭ እንዳይኖረን የተደረግነው በዚህ መንግስት ነው፡፡ ይህም የሰሞኑን የአንድነት፤መኢአድና ሰማያዊ ፓርቲዎች ላይ መንግስት ከምርጫ ቦርድ ጋር በመሆን የደረገውን አ-ዴሞክራሲያዊ አሰራር የመለከተ ሁሉ የሚረዳው ሀቅ ነው፡፡ አይካደም፡፡
- ዜጎች በረሀብና ብስቁልና እየተጠበሱ፤ ስደት ከምን ጊዜውም በላይ ተንሰራፍቶ፤ሀገራዊ ውርደትን እየተከናነብን ባለንበት ወቅት በህዝብ ሀብት በሚተዳደሩ የመገናኛ ብዙሀን የአድገናል ስላቅ የሚሳለቁበት በዚቹ ኢትዮጵያችን ነው፡፡ ይህም አይካድም፤ሰሞኑን እንኳ ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ እያልን በምንኖርባት ሀገር ጠ/ሚኒስተራችን የነፍስ ወከፍ ገቢያችን 631 ዶላር ምናምን ብለው የደሰኮሩት መንግስትና ህዝብ ምን ያህል የተለያዩ ለመሆናቸው ማሳያ ነው፡፡
- ህገ-መንግስቱ በመንግስት አካላት በገሀድ የሚጣስባትና ሙስናና ስራአጥነት ከመቸውም በላይ የገነነባት በዚቹ በኢህአዲግ በምትመራው ኢትዮጵያ ነው፡፡ ይህም እያንዳንዳችን የምንረዳው ሀቅ በመሆኑ አይካድም፡፤
- በሀገራችን ነፃ የሚባልና ህብረተሰቡን በገለልተኛነት የሚያገለግል ተቋም የሌለበት፤ የፍትህ ስርአቱ በገዢው መንግስት የሚዘወር የማጥቂያ መሳሪያ የሆነባትም ይችው በባለ ራእዮች በምትመራው ሀገር ነው፡፤
- በሀገራችን ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ሁኔታ ከአለም ተበዳሪ ሀገራት ከኒጀር ከፍ ብለን በሁለተኝነት ደረጃ የተቀመጥነውም በዚሁ ስርአት ነው፡፡ በብድር በሚገነቡ ጥቂት ፎቅና አስፋልት መንገዶች አድገናል ተመንድገናል ተብሎ፤ በረሀብ የጠወለጉ ቤት አልባ ዜጎች ከየካድሬው ህንፃ ስር የሚተኙባት ሀገርም ይችው የባለራእይ ሀገር ናት!!!


እነዚህንና ዘርፈ ብዙ የአገዛዙ ችግሮችን ነቅሶ ማውጣት በተቻለ ነበር፤ ነገር ግን ሁላችንም የምንኖርበት እውነታና የምንጎነጨው መራራ ፅዋ በመሆኑ፤ መደጋገሙ ‹‹በሰው ቁስል፤……›› እንዲሉ ብሂል ይሆናል፡፡ ዋናው ነገር ግን ዝምታችንና ፍርሀታችን ገደብ አልፎና ገዝፎ የከፋ ባርነትን ሊያጎናፅፈን እየተዘጋጀ ባለበት ሁኔታ ምን እየጠበቅን ነው??? …….ከዚህ የከፋ ባርነትስ ምን ሊመጣ?? …….ሁላችንም ከተሸበብንበት የፍርህ ቆፈን፤ከዘረኛነትና ከጅምላ ፍረጃ አስተሳሰብ ወጥተን፤ ለአንዲት ኢትዮጵያ ብሄራዊ ማንነትና …. ለነፃነታችን በጋራ ልንቆምበት የሚገባ ሰዓት ቢኖር አሁን ነው!!! ……. ከዚህ በላይ ምን እንድንሆን እንጠብቃለን??? ……አበቃሁ፡፡

No comments:

Post a Comment

የምጣዱ እያለ የእንቅቡን፤ የእርስ በርስ ግጭት እና የመንግስት ምላሽ

በያሬድ ሃይለማሪያም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም ግጭቶች መበራከታቸው እና መፈናቀል መቀጠሉ የአገራችንን ፖለቲካ አሳሳቢ እያደረገው እና አገሪቱንም ወደ ችግር ውስጥ እየከተታት ይመስላል። መንግስት ለችግሮቹ የሚሰ...