Wednesday, January 14, 2015

የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ለ16ተኛ ጊዜ ፍርድ ተቀጠሩ ፡፡

በነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ቁጥር #155040 የልደታ ፍርድ ቤት አስራ ዘጠነኛ ወንጀል ችሎት የተከሰሱት 7 የዞን 9 ጦማርያን እና 3 ጋዜጠኖች የፍርድ ሂደት ላይ ፍርድ ቤቱ ይሻሻሉ ብሎ አራት ጉዳዩችን እንዲያሻሽል ለአቃቤ ህግ በተሰጠው ቀጠሮ መሰረት መሰረት አቃቤ ህግ አሁንም አሻሻልኩ ያለውን የክስ ቻርጅ ይዞ ቀርቧል፡፡


አራት መሻሻል አለባቸው ባላቸው ጉዳዮች የሚከተሉት ሲሆኑ
1. በተከሳሾች ተመሰረተ የተባለውን ድርጅት (ቡድን) ለይቶ በግልጽ ማስቀመጥ
2. የእያንዳንዱ ተከሳሽ የስራ ክፍፍል በግልጽ መቀመጥ
3. ተከሳሾች ወሰዱት የተባለው ስልጠና በማን የትና መቼ አንደተከናወነ በግልጽ መቀመጡ
4. ለሽብር ተግባር ውሏል የተባለው 48፣000 ከየት አንደመጣና ለምን ተግባር አንደዋለ በግልጽ ማስቀመጥ ሲሆኑ አሁንም ተሻሻለ የተባለው ክስ ምንም የረባ ለውጥ ሳይኖረው ቀርቧል፡፡

ችሎቱ በብዙ ተጠርጣሪዎች የተሞላ በመሆኑ የተነሳ በጣም ለጥቂት ደቂቃዎች ቆየው ችሎት ክሱ መሻሻል እና አለመሻሻሉን አይቶ ብይን ለመስጠት ለጥር 20 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ በአጭር ተጠናቋል፡፡ በቦታ እጥረት በተባለ ምክንያት ቤተሰብም ሆነ ጓደኛ ወደ ችሎት ውስጥ መግባት የተከለከሉ ሲሆን ሴት ተከሳሾች በፌት ለፌት በኩል ሲገቡ ወንድ ተከሳሾች ግን ከጀርባ በኩል ቤተሰብና እና ወዳጅ እንዳያያቸው ተደርገው ችሎት ውስጥ ገብተዋል፡፡

የዛሬው የክስ ዝርዝር ከቀድሞው የክስ ዝርዝር ምንመ አይነት ለውጥ የሌለው ሲሆን

1. ምንም አይነት ቡድን ወይም የተመሰረተ ድርጅት ለይቶ ሳያስቀምጥ
2. የእያንዳንዱ ተከሳሽ የስራ ክፍፍል ላይ ምንም ለውጥ ሳያደርግ
3. ተሰጡ የተባሉትን ሰልጠናዎች ዝርዝር በማን የት እና መቼ አንደተሰጡ ሳይገልጽ
4. ለሽብር ተግባር ዋለ የተባለውን 48፣000 ብር ማን አንደላከው ( ውጨ የሚገኙ የሽብር ቡድኖች) ሳይገልጽ ተመልሶ ቀርቧል፡፡

No comments:

Post a Comment

የምጣዱ እያለ የእንቅቡን፤ የእርስ በርስ ግጭት እና የመንግስት ምላሽ

በያሬድ ሃይለማሪያም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም ግጭቶች መበራከታቸው እና መፈናቀል መቀጠሉ የአገራችንን ፖለቲካ አሳሳቢ እያደረገው እና አገሪቱንም ወደ ችግር ውስጥ እየከተታት ይመስላል። መንግስት ለችግሮቹ የሚሰ...