ሁላችንም የነፃነትን ካባ እስክንጎናፀፍ ድረስ የኢህአዴግ ህውሀት ስቃይና ዘግናኝ ድብደባ ይቆማል ብዬ ለደቂቃም አስቤ አላውቅም።ዛሬም ወደፊትም እላለው እመነኝ ደርግም ወድቋል ኢህአዴግም ይወድቃል።ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ እየከፈለ ያለው ግፍና ጭቆና ሊሸከመው ከሚችለው በላይ መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው ውድ ጓደኛዬ በላይ ህሊናዬን በመሸጥ ስጋዬን አደላድዬ ልኑር ብል ምን የመሰለ ቪላ ቤትና V8 መኪኖችን በደረደርኩ ነበር። ግን ምን ያደርጋል ያሳደገችኝ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህን እንዳልፈፅም ታግደኛለች " ቦኩ ለግዜ ኩልክሙ"እንዲል መፅሀፍ ልጄ ሁሌም ብትናፍቀኝ የአንድነት ቁርጥ ቀን ታጋዮች በተለይ ወጣቶቹ ሁሌም ቢናፍቁኝ እየከፈልኩት ያለው መስዋት ትግሉን አንድ እርምጃ ያደርሰዋል ብዬ ገምታለው። ነገር ግን በላይ ዕለት በዕለት እየሰማሁት ያለው የወጣቶቹ ቅራኔ አንተና ካቢኔህ ለይስሙላ የተቀመጣችሁ እስከማለት ደርሻለው። በተለይ በስዩም፤ በዘካሪያስ፣ በእመቤት ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎች አለመመለስህ እምነትህ ተሸርሽሮ የጋን ውስጥ መብራት ሆነሀል። ለምንድነው ወጣቶች ሊጠይቁኝ መተው በእንባ ስለጠቀስኳቸው ግለሰቦች የሚያወሩኝ? በእውነት ስዩምና ዘካሪያስ ይመጥናሉ ብለህ ነው ያስቀመጥካቸው? ወይስ ትዋሸኝ ነበር አብረን ስናወጋ ፀጋዬስ ይህ ሁሉ ሲደረግ የት ሄዶ ነው? ወይስ የተፈለገው የኔ መወገድ ነበር በእውነት በጣም አዝኛለው። አስራት አብርሀምስ ቢሆን ያለ ግዜው ምነው ቁጭ አደረከው? በንግግር ክህሎታቸው የሚያሳምኑ እንደ አበበ አካሉ፣ አስራት ጣሴ የሉም? አስራትን ማድረግ የነበረብህ ፓለቲካ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚ አንዱ ዘርፍ ላይ አስቀምጠህ እንዲፅፍና የምርምር ስራ እምዲሰራ ማድረግ ነበረብህ ግን ምን ያደርጋል ወረቀት መበተን አይደለም ለተልዕኮ እንኳን ቦቅቧቋ የሆኑትን እነ ዘካሪያስን መምረጥህ በቅርቡ የእጅህን ታገኛለህ። የተከበራችሁ የአንድነት ፓርቲ አባላት በተለይ ወጣቶቹ በምንም መልኩ ቢሆን የተስፋ መቁረጥ ስሜት እንዳይታይባችሁ አጭበርባሪዎችንና አስመሳዮችን ታገሏቸው አንድነት የሁላችንም ነው። እኔ እየከፈልኩት ላለው መስዋዕት አንዳችም አይከፋኝም በተለይ አብዛኛው የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት ምን እንዳረኳቸው ጠይቁልኝ? ቢያንስ ቂሊንጦ መምጣት ቢያቅታቸው የቀጠሮዬ ቀን ቢመጡልኝ ለኔ ብርታት ለልጄና ለባለቤቴ ፅናት እንደሚሆን አልጠራጠርም። ስለዚህ በላይ ፓለቲካ በይሉኝታ የሚመራ ሳይሆን በብቃት እንደሆነ ልታሳይ ይገባል። በምንም መልኩ እነ ዘካሪያስ ለፓርቲው የሚመጥኑ አይደለም በተለይ ለአመራርነት ከመዐድ ጀምሮ ሲቀጥል ከመኢአድ እንዴት የክህደት ካባቸውን አያጠለቁ የኢትዮጵያን ህዝብ መከራና ስቃይ በፍርፋሪና በማይጠቅም ገንዘብ እየሸጡት እንደሆነ እኔም አንተም የምናውቀው ብዙ ጉድ አለ ወጣቶቹ የነገሩኝ ጉድ ብዙ ቢሆንም ለፓርቲው ህልውና ስል ትቼዋለው።ብዙ የደንብ ጥሠትና አምባ ገነንነት በፓርቲው እየተበራከተ የሰራተኞች ቅጥር.....ብዙ ብዙ ብለውኛል ምናልባት ስሜታዊ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ ስላሰብኩኝ እውነታውን አንተ ድረስበት ለዛሬ ይብቃኝ፤ ድል የህዝብ ነው እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርካት አሜን።
Like
No comments:
Post a Comment