የተጠቀለሉት ጠቅላይ በአንድ ማሕበረ ሰብ በክብር እንግድነት ተገኝተው ነበር ።
እናም የሀገሪቱ መሪ እንደመሆናቸው ሁሉ ባገኙት አጋጣሚ ለተሰበሰበው ሕዝብ መንግሠታቸው ምን እየሠራ እነደሆን በይፋ ያጋለጡበት ቀን ነበር ማለት ያስችላል ፣ ያች ቀንም እነደ አንድ የታሪክ አጋጣሚ ተደርጎ ሲዘከር ይኖራል ።
እኔ በበኩሌ ጠቅላዩን መርቄአቸው አለሁ ።
ለምን እንደምትሉኝ አውቃለሁ በኢህአዴጋውያን ፍልስፍና የሚገዟትን ሀገር ፣ የሚገዙትን ሕዝብ እንዴት ማዋረድ (ኢንሳልት) ማድረግ እንዳለባቸው በሥልጠና መልክ በዝግ ስብሰባ በሕውሓቶች የሰጣቸዋል ። ከተሰጣቸው ስልጠና ውጭ በቅንነት ሕዝብ የሚፈልገውን መናገር ወይም መተግበር አይችሉም ። ያን መመሪያ የተላለፈ ካድሪ መዘዙ አስከፊ መሆኑን ከተሞክሮ ያውቁታል ። ብዙዎቹን የትግል አጋሮቹን( ጓዶቹን) እየበላ የመጣ ድርጅት መሆኑን ጠንቅቀው ያውቁታል ።
ስለዚህ የተጠቀለሉት ጠቅላይ ያን እውነታ ነበር ይፋ ያደረጉት ።
አወ ጠቅላዩ እንዳሉት በመንግስት ደረጃ የወጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ የተቀመጠችው ቃል “ጥቅስ ” « ገረድ » የምትል ተቀምጣለች ብለውናል ።
ታዲያ በፖሊሲ ደረጃ ወደግርድና እንዲሄዱ በሰው ንግድ ላይ ለተሰማሩት ነጋዴዎች ፈቃድ ሰጥቶ ግርድና ተብለው ከሚሰደቡት የለጋ እድሜ የልጅነት ጊዜ የተወሰደባቸውን እህቶቻችን ላይ በአባይ ግድብ ሥም ገንዘብ መለመኑን ምን እንበለው ? « ለማኝ » አዎ ለማኝ በልቶ አይጠግብ ስግብግብ ።
አቶ ኃይለ ማርያም ሆኑ አቶ አለምነህ መኮነን የተሰጣቸው ወይም የሰለጠኑበትን ወደተግባር የቀየሩበት እንጅ ከሕሊናቸው አፍልቀው ከአፋቸው አውጥተው ከራሳችው አይደለም ።
ከበስተኋላ አስገዳጅ ከለለው በስተቀር ከሕዝብ ፊት ቁሞ ሕዝብን በጅምላ የመስደብ ሞራሉም ድፍረቱም የት ተገኘ ብሎ መገመቱ ቀላል ነው ።
በዓለም ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት ይህን አይነቱ ምልክት ተከስቶ ነበር ከዛ ነው ፖለቲከኞች ትሬንፕ ላይ ብቅ የሚሉት ከሰባ ዓመታት በፊት በአውሮፓ ምድር የፀረ ሴማውያንን እንቅስቃሴ ተመልክቶ አዶልፍ ሂትለር ትሬነፕ ላይ የወጣው ከሀያ ዓመታት በፊት በሩዋንዳም በቱሲዎች ላይ የተወሰደው የዘር ማጥፋት ልክ እንዳሁኑ በኢትዮጵያ በሕውሓት ተጠንስሶ በአንድ ዘር በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ላይ የጥላቻ ዘመቻ በትምህር በስልጠና እየተሰጠ አንዳን ቦታ ውጤቱ ፍሬ አፍርቶ ተመልክተናል ።
አቶ ጠቅላይ ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው በዛ ብሔር ላ ቋንቋውን ብቻም ሳይሆን የተለየ ቀለም እንዳለው ጠቅሰውታል ።
ከሁሉም በላይ እኔም በዚህ አጋጣሚ ለማለት የፈለግሁት ከላይ የጠቀስኩት ጥፋት እንዳይከሰት መሰራት ያለበት አሁን ነው ።
ከተፈፀመ በኋላ ለሚሊየኖች መታሰቢያ ማቆሙ ሀውልት መሥራቱ በየዓመቱ የሙት መታሰቢያ ማድረጉ እርባና የለውም ።
ኢትዮጵያዊ ነኝ የምንል በኢትዮጵያ የምናምን ከሆነ መቃወም ያለብን አሁን ይመስለኛል ጥይት መጮህ ከጀመረ ማስቆሙ ይከብዳል ።
ምሁራን በተለይ ካለፈ በኋላ ታሪክን ለመፃፍ ፊልሙን ለመሥራት ታስቡ ይሆናል?
አይደለም እየሰማችሁ እያያችሁ አሁን ምን አገባን ያላችሁ ሁሉ ከህሊና ወቀሳ አትድኑም እላለሁ።

No comments:
Post a Comment