By #ሚስጥረ_ካድሬ
ህዳሴ ምንድን ነው ፤ ምንድነው ህዳሴ ?
ዛሬ በአንድ ወቅት ያጋጠመኝን አንድ ቆንጆ ውርደት ላጫውታችሁ ቆርጬ ተነስቻለሁና ውርደቴን ታነቡልኝ ዘንድ በታላቁ ግድባችን ስም በጠመንጃ እጠይቃችኋለው፡፡
ግዜው እንደ ወያኔ አቆጣጠር 19 ምናምን ላይ ነበር፡፡ በኢህአዴግዬ አበል የገዛሁትን ሱፍ ግጥም አድርጌ ለብሼ ከመድረክ ላይ ስብሰባ ልመራ ተኮፍሼ ተዶልቼያለሁ፡፡ ስብሰባውን ባማረና በደመቀ መልኩ እየመራሁ ሳለ ድንገት ሰይጣን አሳስቶኝ ወደ ታዳሚያኑ አይኔን አፍጥጬ ጥያቄ ካልጠየቃችሁኝ ብዬ እንዲህ በማለት ቀባጠርኩኝ፡፡ “እስቲ አፈችሁን አትለጉሙት! ምንኣባታችሁ ይዘጋችኋል! ጥያቄ አለመጠየቅ እራሱ እኮ ኪራይ ሰብሳቢነት ነው! ስለዚህ የህዳሴያችንን ተሀድሶ ለዜጎቻችን ለማብሰር ጥያቄ መጠየቅ አለብን! ህዳሴያችን ሊሰምር የሚችለው በጥያቄ ነው! ያለ ጥያቄ ህዳሴ የለም!. . .” ይህንና የመሳሰሉትን ልማታዊ ቃላት ለፍልፌ ሳበቃ ጠያቂ ፍለጋ አይኖቼን ወደ መድረኩ አማተርኩ፡፡ ግና ጠያቂ ከየት አባቱ ይምጣ፡፡ እኔም እነዚ ፀረ-ጥያቄ ሀይሎች ደሜን አፍልተውት ኖሮ ድምፄን ከቅድሙ ይበልጡኑ ከፍ አድርጌ ዲስኩሬን እንዲህ በማለት መልቀቅ ጀመርኩ፡፡
“እውነት እላችኋለው ይሄ አመላችሁ ሀገራችንን ወደ ኋላ ከመጎተት ያለፈ አንድም ሀገራዊ እንድምታ የለውም፡፡ እንዲህ እንደ እናንተ ያሉ ጥያቄ ቢሶች ባይበራከቱ ኖሮ ሀገራችን ኢህአዴግ ማለቴ ሀገራቸን ኢትዮጲያ በሺ ዲጂት ባደገች ነበር፡፡ ሆኖም እናንተ በክፉ ልቦና ተነሳስታችሁ፤ ድብቅ ፖለቲካዊ አጀንዳችሁን አንግባችሁ ፤ ለርካሽ ግዜያዊ ጥቅም ስትሉ የህዳሴውን ጉዞ ለማደናቀፍ ቆርጣችሁ ተነስታችኋል፡፡ ህገ-መንግስቱንም በአደባባይ ንዳችሁታል፡፡ ስለዚህ እናንተ አሸባሪዎች. . . ወይ ጠይቁ ወይ ደግሞ ህዳሴውን ለማስቀጠል ሲባል ለምወስደው ማንኛውም አይነት እርምጃ ሃላፊነቱን አልወስድም፡፡”
አሁንም ንግግሬን እንደጨረስኩ ታዳሚውን ገላመጥኩት፡፡ ንግግሬ አስደንግጦዋቸው ነው መሰለኝ ጥያቄ ለመጠየቅ ሁሉም እጁን አወጣ፡፡ የያንዳንዱን ካድሬ እጅ ለ 5 ደቂቃ ካየሁ በኋላ የአንዲት ቆንጅዬ ካድሬ እጅ ላይ አይኔም ልቤም አረፈ፡፡
“እሺ የኔ እህት ያው እንደምታውቂው ህዳሴያችን ለሴቶች ቅድሚያ ስለሚሰጥ እባክሽን ጠይቂኝ” አልኳት
እሷም” እድሉ ስለተሰጠኝ አመሰግናለሁ” አለች
እኔ---- ምንም አደል
እሷ--- በተደጋጋሚ ህዳሴ የሚል ቃል ስትጠቀም ሰምቼሀለው፡፡ ግን ትርጉሙ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ እናም እባክህ ከቻልክ ብታብራራልኝ
እኔ---(ብዙ ግዜ ስጠቀምበት የማውቀው ይመስለኝ ነበር ግን ባስብ ባስብ ሊመጣልኝ አልቻልም ከዛም ወደልጅትዋ ዞር ብዬ) እንግሊዘኛ አታቂም እንዴ አልኳት
እሷ-----አረ አቃለው
እኔ----- ታድያ እንዴት እስከ ዛሬ ህዳሴ ማለት ምን እንደሆነ አታውቂም
እሷ----- አረ ህዳሴ የሚል ቃል እንግሊዘኛ ላይ የለም
እኔ----- ታደያ እኔ ከየት አመጣሁት
እሷ------ እኔ ምን አውቃለሁ
እኔ------(ንዴቴን መቆጣጠር አቅቶኝ) እንዲሁ ስትታዪ እራሱ ሰርጎ ገብ ነገር ነው ምትመስይው፡፡ እንዴት እስከ ዛሬ ህዳሴ ማለት ምን ማለት እንደሆነ አታውቂም
እሷ----- እሺ እርሶ ካወቁ ይመልሱልኛ ታድያ . . .
እኔ------ እፍሽን ዝጊ አንቺ አሸባሪ
እሷ------- የመጠየቅ መብት አለኝ እኮ፡፡ ደግሞም እርሶ እራሱ. . .
እኔ------- እንደውም ህገ-መንግሰቱን እየተፃረርሽ ስለሆነ ለዛሬ አበል አይሰጥሽም፡፡ ሁለተኛ ጥያቄ እጠይቃለው ብትዪ እጣ ፈንታሽ ቃሊቲና ቂሊንጦን እንደሞሏት ነገረኞች ነው የሚሆነው፡፡
እሷ--------- ታዲያ ለምን ጠይቂ አሉኝ
እኔ----------- እንጃባሽ! አንቺ ቅማላም ካድሬ! አዋረድሽኝ ዛሬ፡፡
------------------------// //---------------------------------

No comments:
Post a Comment