በታክሲ ጉዞ ላይ ነኝ ሁለት ከኔ በስተኋላ ከተቀመጡት ተሳፋሪውች አንዱ ምሬቱን ይገልጻል፤-
.. ቆይ እኛ ግን ለታክሲ ተሰልፈን፣ ለዳቦ ተሰልፈን፣ ከሀገር ለመውጣት ተሰልፈን እንዴት እንችለዋለን?
ሌላኛው ተሳፋሪ ቀበል አደረገና
.. አይዞህ!.. ይሄ ብዙም አይግረምህ ከዚህ በኋላ ገና ተሰልፈህ ትረሸናለህ፡፡… ተሳፋሪው በሳቅ…
ለማንኛውም ከሰነበትኩበት ስፍራ ተመልሼ ሸገርን ስረግጥ ወሬን እያወራ ያለ አፍ ሁሉ በአንዲት ታዳጊ ልጅ ስም ተይዞአል፡፡ ራድዮ ወልያ ፌስ ቡኩ ወሬ ስላገኙ ይሁን አልያም ሀዘኔታ ገብቷቸው ባለየለት መልኩ ታሪኩን እያርገበገቡት ደረስኩ፡፡ በእርግጥ እኔም ከሰማሁት እንዲሁም ካነበብኩት የታዳጊዋ ታሪክ ተነስቼ የደረሰው ጉዳት እጅጉን አሳዝኖኛል፤ ድርጊቱም እንስሳነት በሰው መልክ የተገለጠም ይመስል ነበር፡፡ ከምንም በላይ ግን አሳዛኝነቱን የሚጨምረው ተጠቂዋ ይህች ታዳጊ ብቻ አለመሆኗና ብዙ እህቶቻችን በየጓዳቸው አፍነው የያዙት ተመሳሳይ አንዳንዱም ባስ ያለ ስቃይ መኖሩን ስናስብ ነው፡፡ ታዲያ አንዱ ጓደኛዬ የሌሎችን ታሪክ አንስቶ ‹‹ይህ እኮ አዲስ አይደለም የተለመደ ነው›› ቢለኝ ተናድጄ ሰደብኩት፤- አንተ የለየልህ ክፉ ሰው ነህ! “ኢህአዴግ”… አልኩት፡፡
ብቻ ይህ አይነት ድርጊት የት ጋር እና እንዴት እንደሚቆም ባይገባኝም፤ እኔ ጉልበት አለኝ… ገንዘብ አለኝ… እንትንና ይሄን ማድረግ እችላለሁ ከሚል እራሳችንን ከፍ ካደረግንበት የባዶ የበላይነት ላይ ሲወረድ ይመስለኛል፡፡ እንዲሁም አንዳንዶች እንደሚሉት ለእዚህ አይነቱ ድርጊት መደጋገም የፍትህ አካል የሚሰጠው ዳኝነት ደካማ መሆን እና ወንጀለኛን ከጥፋተኛው ለይቶ መቅጣት ያልቻለ የፍርድ አሰጣጥ ስነስርዓት መኖሩ እንዲሁም ፍርድ ቤቶች በመንግስት ጫና ስር መውደቃቸው መረጃ ላይ የተመረኮዘ አሰራርን ሳይሆን ተጠርጥረው ነው የተያዙት በሚባሉ ግለሰቦች ላይ መንግስት ፍትህ ሰጪ መሆኑን ለማሳየት ያለ በቂ ማስረጃ ማስፈረዱን ለችግሩ እልባት እንዳያገኝ የከለከለው ይመስለኛል፡፡
.
አንዱ ወዳጄ እንዲህ አለ
ኢህአዴግን የተሸከመ ትከሻ ስቃይ ምን ማለት እንደሆነ እንዴት ይጠፋዋል?››

Robel Ayalew
No comments:
Post a Comment