Thursday, October 23, 2014

በቂሊንጦ ማረሜያ ቤት የማረሜያ ቤቱ ሀላፊዎችና የደህንነት አካላቶች ቅዱሳን መፃሀፎችንና የታራሚዎች የፍርድ ቤት ማስታወሻዎችን ማቃጠላቸው ታወቀ ::



ሰኞ እለተ ጥቅምት 10 2007 በቂሊንጦ ማረሜያ ቤት ቅዱሳን መፃሀፍትና የታራሚ ንብረት የሆኑ መፃሀፍቶችና የታራሚዎች የፍርድ ቤት ማስታወሻዎች ከሶስቱም ዝሆኖች ሰብስበው እንዲቃጠሉ መደረጋቸው ታወቀ።እነዚ መፃሀፎች በማረሜያ ቤቱ ሳንሱር ተደርገውና አልፈው የሚገቡ መፃሀፎች ሲሆኑ በሶስቱም የማረሜያ ቤቱ ዞኖች ቤተ መፃሀፍት ይገኛል።ይሁን እንጂ በየዞኖቹ በታራሚዎች እጅ የሚገኙትን የእምነት መፃሀፍትና ቅዱሳን መፃሀፍትና የታራሚዎች የግል ማስታወሻዎች እንዲቃጠሉ በማድረግ የማረሜያ ቤቶቹ አስተዳደሮች አቻ የሌለው እኩይ ተግባራቸውን ፍፅመዋል።

ይህ የማረሜያ ቤት ኢ ህገ መንግስታዊ ድርጊት የማረሜያ ቤቱ አስተዳደሮች በራሳቸው ፍቃድ የሚያከነውኑት ሳይሆን መንግስት ሆን ብሎ በነሱ በኩል የሚያስፈፅመው ኡክይ ተግባር መሆኑ በግልፅ ያሳያል ለዚህም ማሳያ ባሳለፍነው የተከበረው የረመዳን ወር መንግስት በንፁሀን ኢትዬዺያወያን ሙስሊሞች ላይ የአይሁድ ተልኮን ለማሳካት በወሰደው መንግስታዊ ሽብር (ጥቁር ሽብር)እለት ብዙ እስላማዊ መገለጫ የሆኑ ሂጃቦች ኮፊያና የመሳሰሉ የእምነት መገለጫ የሆኑ ነገሮች መቃጠላቸው የሚታወስ ነው አልፎም በርካታ ምእመናንን ለአካል ጉዳት የዳርገ አረመኔያዊ ድርጊት በመንግስት ታጣቂ ሀይሎች የተፈፀመ ሲሆን ከሁሉ በላይ የምእመናኑን ስነ ልቦና የነካና ፍፁም ከአእምሮ ሊፋቅ የማይችል ታላቅና ዘግናኝ ኢ ህገ መንግስታዊ የሆነ ተግባር. የሆነና የሀይማኖቱን ተከታዬች ፍፁም ያስቀየመ እንዲሁም የዚህን ስራአት ሸፍጠኝነት በጉልህ ያሳየ ተግባር ፍፅመዋል።

ይህ ሙስሊሞች የተፈጠሩለትን አላማ ያነገበውንና ለሰው ልጆች ሁሉ መመሬያ ሆኖ የተወረደውን የተከበረው ያአላህ ቃል የሆነውን "ቁርአን" ማቃጠላቸው ይታወሳል ።በሳለፍነው ሳምንትም በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኔዬ በተለምዶ ዘነብ ወርቅ አካባቢ እንዲሁ ቁርአንና መፃሀፍ ቅዱስ ገንዳ ስር ተጥሎ መገኘታቸው የሚታወስ ሲሆን እነዚህ ሁሉ እምነት ላይ ያነጣጠሩ ዘመቻዎች በህዋት መረሹና እምነት የለሹ እምነቱን አቢዬቶ አድርጎ በሚገዛው የኢሀዲግ መንግስት ተጠናክሮ ቀጥሎዋል።

ሰሞኑን በቂሊንጦ ማረሜያ ቤት ቅዱስ መፃሀፍትን በማቃጠል የተደረገው ኢ ህገመንግስታዊ ድርጊት ታራሚዎችን ከአካልም ባለፈ በስነ ልቦናም ጫና ለማሳደርና ታራሚዎች በቂ የሆነ እውቀት እንዳይኖራቸው ሆን ተብሎ ታስቦ የተደረገ አረመኔያዊ የሆነ መንግስታዊ ሽብር ነው።ይሄ ደሞ አንድ ሀገርን አስከብራለሁ የዜጎችንና የሀይሞኖትን ነፃነት አስከብሪያለሁ ከሚል መንግስት የሚጠበቅ ተግባር. ባይሆንም ህዝቦቹን በማሰቃየት የመንፍስ እርካታ የሚያገኝው እንዲሁም የዜጎችን መሰረታዊ መቶች በመጣስ ወደር የሌለው የዚህ ስራአት ባለ ቤት የሆነው ህዋት መራሹ የወያኔ መንግስት ኢሀዲግ በማን አለብኝነት ስሜት እየፈፀመው ይገኛል. ታዲያ እነዚህ አካላት ዝም ሊባሉ አይገባም ሁሉም ነገር ይታለፋል ነገር ግን የሰው ልጅ የተፈጠረበትን አላማ ለመንጠቅ የሚደረግ ሙከራና ተግባር ሊቆም ይገባል ልብ ያለው ልብ ይበል!!!!

ቢቢኤን ሀሙስ ጥቅም 12 2007

No comments:

Post a Comment

የምጣዱ እያለ የእንቅቡን፤ የእርስ በርስ ግጭት እና የመንግስት ምላሽ

በያሬድ ሃይለማሪያም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም ግጭቶች መበራከታቸው እና መፈናቀል መቀጠሉ የአገራችንን ፖለቲካ አሳሳቢ እያደረገው እና አገሪቱንም ወደ ችግር ውስጥ እየከተታት ይመስላል። መንግስት ለችግሮቹ የሚሰ...