የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የዲፕሎማሲ ደህንነት ክፍል ዛሬ ባወጣው አስቸኳይ መልዕክት በአዲስ አበባ የሚገኙ የአሜርካ ዜጎች ብዙ ሰዎች የተሰበሰቡባቸውን: ኢትዮጵያዊያንና የውጭ ዜጎች ከሚያዘወትሯቸው ቦታዎች እንዲርቁ አሳስቧል::
ኢንባሲው የደረሰው የአደጋ መረጃ አልሸባብ የቦሌን አካባቢ ለማጥቃት እንዳሰበ ይገልጻል:: በቦሌ አካባቢ የሚገኙ ምግብ ቤቶች: ሆቴሎች: ምሽት ቤቶች: የአምልኮ ቦታዎች: ትላልቅ የሸቀጥ ሱቆችና: ሞሎች የሽብር ሴራው ኢልማዎች ሊሆኑ ስለሚችሉ ዜጐች ከእነዚህን ተቋማት ሌላ ማሳሰቢያ እስከሚወጣ ድረስ ገለል እንዲሉም ያሳሰባል::
አደጋው ሊጣል የታሰበበት ትክክለኛ ቦታ በእርግጥ ስላልታወቀ የአሜሪካ ዜጎች ነቃ ብለው የግል ደህንነታቸውን እዲከታተሉም በመጨመር ያሳስባል::
ምንጭ:- OSAC
No comments:
Post a Comment