አንድ ሚኒስትር የነበረ ካድሬ ዛሬ መንግስቱ ሐ/ማሪያም ምንም የፓለቲካ እውቀት የሌለው ሰው ነው " ሲል ተቸ:: ስድቡን ሲጨርስ ከአዳራሹ ውስጥ ብዙ እጆች ለጥያቄ ወጡ አንድ ተማሪ ብቻ እድል ተሰጠው ቀጠለ " እኔ የደርግ ስርአትን እቃወማለሁ ተመልሶም አይመጣም እውነታውን እንየው መንግስቱ በ 19 አመቱ አሜሪካ ሄዶ ፓለቲካ ሳይንስ ተምሮ የመጣ ነው:: መለስ ግን ከ አ.አ ዩኒቨርሲቲ ስለተጫረ (ወድቆ ሲባረር) በረሃ የገባ ሰው ነው ጎበዝ ተማሪ እንደነበር የነገረን ETV ነው:: የኢትዮጲያ ህዝብ ደግሞ ETVን አያምንም:: እኛ ሳቅን
ልጁ ቀጠለ " መንግስቱ የአንድ ብሔርን የበላይነት ሳይሆን እኩልነትን ነው ያሰፈነው በመለስ ጊዜ ከ ህዳር 29 ውጪ ምን እንደሚሰራ እናውቃለን
መለስ በጥሩ ሁኔታ አገሪቷን መርቷል የሚል አመለካከት የለኝም ምክንያቱም ቤተሰቡን በስነ-ስርአት መምራት ያልቻለ አገር ይመራል ብዬ አላስብም የመለስ ቤተሰቦች ይቅርታ አርጉልኝና ሰካራሞች ናቸው:: ልጁ አሁን ዲቃላ ሁሉ እንደወለደች ሰምተናል እስከ እኩለ ለሊት ታዋቂ የሚባሉ ጭፈራ ቤቶች ስትጨፍር ታነጋለች ገንዘቡ ከየት መጣ ቢባል ምንም ጥያቄ የለውም በህዝብ ገንዘብ እንደምትጨፍር የታወቀ ነው:: ታዲያ አትነግድ ወይ አታርስ ::
እርግጥ ነው ደርግ ስህተቶችን ሰርቷል እነዛን ስህተቶች ኢህአዴግ አጠናክሮ ቀጥሎባቸዋል ለውጥ ካላችሁኝ የስም ለውጥ ብቻ ነው ያለው :: ደርግ ተማሪዎችን ረሽኖአል ኢህአዴግም ተማሪዎችን እረሽኖአል እየረሸነም ነው
ቀበሌዎች በደርግም በኢህአዴግም የመጨቆኛ መሳሪያ ናቸው:: እኔ ኢህአዴግ በምርጫ ሲሸነፍ ስልጣን ይለቃል ብዬ አላስብም ጨርሻለሁ:: "
No comments:
Post a Comment