Wednesday, April 17, 2019

የምጣዱ እያለ የእንቅቡን፤ የእርስ በርስ ግጭት እና የመንግስት ምላሽ

በያሬድ ሃይለማሪያም

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም ግጭቶች መበራከታቸው እና መፈናቀል መቀጠሉ የአገራችንን ፖለቲካ አሳሳቢ እያደረገው እና አገሪቱንም ወደ ችግር ውስጥ እየከተታት ይመስላል። መንግስት ለችግሮቹ የሚሰጠው ትኩረት እና ፈጣን ምላሽ እንዲሁ አጠያያቂ እየሆነ ነው። በብዙዎቹ አካባቢዎች ግጭቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ቅድመ ምልክቶች እየታዩ አፋጣኝ እርምጃ ሲወሰድ አይስተዋልም። ከዛም አልፎ ግጭቶቹ ተከስተው ሰዎች ከሞቱ፣ በሺዎች ከተፈናቀሉ እና ወደ ለየለት ቀውስ ካመራ በኋላ ነው የፌደራል መንግስቱ ጣልቃ ገብቶ እርምጃ ሲወስድ የሚስተዋለው።

በአብዛኛዎቹ ግጭቶችም የመንግስት ባለሥልጣናት በአንድ ጉዳይ ላይ እርስ በርሱ የሚጣረስ መግለጫ ሲሰጡ መስማት የተለመደ ሆኗል። ከዛ ይልቅ ከመንደር ካድሬ እስከ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ድረስ ለግጭቶቹ መስፋፋት ማህበራዊ ድህረ ገጽ ትልቁን ድርሻ እንደተጫወተ ሲናገሩ እና በመገላጫ ሲጠቅሱ ማየት ሌላው አስገራሚው ጉዳይ ነው። አገሪቱ ጽንፍ በያዙና ጠርዝ በረገጡ፣ አፍንጫቸው ድረስ በታጠቁ አክራሪ ቡድኖች እየታመሰች እውነታውን እዛው መጋፈጥ ሲገባ ችግሩን ከማህበረ ድረገጾች ጋር ማያያዝ በፍጹም አግባብነት የሌለው፣ የራስን ኃላፊነት ካለመወጣት የሚመጣውን ተጠያቂነት ወደጎን የተወ እና የአፈና ዳርዳርታ ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ የትኛው የኢንተርነት አገልግሎት ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ይህን ያህል ለግጭት በሚዳርግ ደረጃ ለቅስቀሳ የዋለው? እንኳን ግጭቶቹ በተቀሰቀሰባቸው ገጠራማ የአገሪቱ ክፍሎች አይደለም በመሃል አዲስ አበባ እንኳ ያለው የኢንተርኔት ሽፋን ይህን ያህል የሚያስደነፋ አይደለም። ሰሞኑን በኦነግ ታጣቂዎች እየታመሱ ያሉት ከደብረብርሃን እስከ ደሴ ያሉ ከተሞች እና መንደሮች አካባቢ የኢንተርኔት አገልግሎት እንኳን ሰውን ለጭት ለማነሳሳት ይቅርና ሕዝቡ የደረሰበትን በደል አቤ እንዳይል እንኳ ግንኙነቶች ተቋርጠው እንደነበር እና ወትሮውንም ያን ያህል የኢንተርኔት አገልግሎት በበቂ ሁኔታ በአካባቢው ያልተዳረሰ መሆኑ ይታወቃል።

መሬት ላይ ያለውን እውነታ ከመጋፈጥ ይልቅ በየመግለጫው ግጭቶቹ በማህበራዊ ድህረ ገጾች በሚደረጉ ቅስቀሳዎች እና የጥላቻ ንግግሮች እንደተጀመረ ወይም እንዲባባስ እንደተደረገ አድርጎ መግለጽ አሳፋሪ ነው። የጥላቻ እና ጸብ ቀስቃሽ የሆኑ ንግግሮችን የሚቆጣጠረው ሕግ አስፈላጊነትን ለማጉላት ከሆነ እዛ ላይ ብዙም ባትደክሙ ጥሩ ነው። አስፈላጊነቱ በሕዝቡም ዘንድ ታምኖበታል። ከዛ ይልቅ መንግስት መጀመሪያ የተጣለበትን ሰላም እና ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ ስላልሆነ ሌላ ምክንያት ካላቸው ንገሩን። ከሌለም ኃላፊነታችሁ በአግባቡ ተወጡ።

መንግስት የዜጎችን ደህንነት ያስጠብቅ። የከረረ ብሔረተኝነት ከነፍጥ ጋር ሲገናኝ ተቀጣጣይ ፈንጂ ስለሆነ መጨረሻው መተላለቅ ነው። ይሄ ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያ ያመጣው ጣጣ ሳይሆን አገሪቱ ለአርባ መታት የተነደፈችው መርዝ እና ሥርዓቱ ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት ኮትኩታ ያሳደገው ዛፍ ፍሬ ነው። የእነ ኦነግም የጥላቻ ፖለቲካ የአርባ አመት ሥራ ውጤት ነው። ሶሻል ሚዲያ ሳይኖር በፊት እነ አርባጉጉ፣ በደኖ እና አርሲ ላይ እና በቅርቡም ቡራዩ ላይ በኦነግ ታጣቂዎች የተፈጸሙትን የዘር ማጥራት ወንጀሎች ታዝበናል።

መሬት ላይ ያለውን አክራሪ ብሄረተኝነት በሕግ ቁጥጥር ስር ማድረግ ሳይቻል አየር ላይ ስላለው ማህበረ ድረገጽ ደጋግሞ ማውራት የምጣዱ እያረረ የእንቅቡን እንደ እንደ ማገላበጥ ነው የሚሆነው።

ቸር እንሰንብት!

Tuesday, March 5, 2019

በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እየትመራ ያለው አዲሱ መንግስት እንደ መንግስት መቆጠር የለበትም



አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣንን ከተቆጣጠሩት በኋላ የአነስተኛ ብሄረሰብ ግጭቶች እንደ ሰደድ እሳት ጨምረዋል የዘር ጥላቻ በሰዎች ልብ ውስጥ እያደገ ነው በተለያዩ ጎሳዎች መካከል የሚደረጉ ግጭቶች በመንግስት በሚጠቀመው የጎሳ-ነክ ፖሊሲዎች ቀጥተኛ ውጤት ናቸው ። ብዙ ንጹሐን ሰዎች በተለይም ህጻናት እና ሴቶች ሕይወታቸውን አተዋል።.


ሰውች በብሄራቸው ወይም በሚናገሩበት ቋንቋ ምክንያት መድሎ እየጨመረ ነው.። የዘር ማጥፋት ዘምቻ በድብቅ እየተደረገ ነው። እንዲህ ዓይነቱ ባህሪያት በመንግስት መታገዝ እና መበረታታት ቀጥለዋል። የአሁኑ ፖሊሲዎች በአብዛኛው ሰዎችን በአንድ ላይ የሚያመጣውን የጋራ ነገሮቻችን ከመንከባከብ ይልቅ ልዩነቶችን የሚያጎሉ ናቸው።

ገዥው አካል ገዳይ እና ዘረፊ ቡድን ነው ። በውጭ በዲሞክራሲ ሽፋን ላይ የውሸት ምስሎችን የሚሸፍኑ አሻንጉሊት ወይም የውሸት ተምሳሌት ናቸው። ይህ ቡድን እንደ መንግስት ሊታይ አይገባም ምክንያቱም ሁለት አስፈላጊ ነገሮች አያሞላም።


1 መንግስት እንደ መንግስት የዜጎቹን መብት በእኩልነት ማስፈን አለብት ፣ ዘር እና ጎሳን መስርት ሳያድርግ

2 መንግስት እንደ መንግስት የሃገር ድንብር ማስጠበቅ አለብት



ሰለዚህ አዲሱ መንግስታችህ እንደ መንግስት እነዚህን ያደርገ አይደልም ።


ይህ ገዳይ እና ዘራፊ ቡድን ሁለቱንም መስርታዊ ነገሮችን አይሞላም እና አዲሱ መንግስት እራሱ የህጋዊ ሽብርተኝነ ነው። ለማንኛውም አንድ ነገር ልናገር በማንኛውም መንገድ አዲሱን መንግስት የሚደግፍ እያንዳንዱ ሰው ወይም ሃገር ለአገሪቱን ለጅምላ ጭፍጨና ለሃገሪቱ ነዋሪዎች መፈናቀል ድጋፍ እንደሚሰጥ መዘንጋት የለበትም።

ሃገራችንን እንደሃገር ለማቆይት ይሄንን ዘርኛ መንግስት ታገለን መጣል አለብን በአንድነት።

Thursday, February 14, 2019

የዶ/ር አብይ አመራር እና የሰብዓዊ መብት ጉዳይ!



አሮጌው ህወሃት መራሽ ኢህአዴግ ከአዕላፍ ነቀፌታዎቹ አንዱ በሰብዓዊ መብት ላይ ያለው እንደ ዱር አውሬ የሚቃጣው አቋሙ ነበር፡፡ ኢህአዴግ በራሱ ህዝብ ላይ ያደረሰው አረመኔያዊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዓለም ላይ በእርኩስነታቸው ከሚታወቁ መንግስታት መደዳ ቀዳሚው ሳያደርገው አይቀርም፡፡ ቀዳሚ የሚሆንበት አበይት ምክንያት በዓለም ታሪክ ብቅ ብለው የነበሩ እንደ ናዚ ያሉ ጨካኝ መንግስታት የጭካኔ በትራቸው ያረፈው በራሳቸው ህዝብ ላይ ሳይሆን “ሌላ” በሚሉት ህዝብ ላይ ስለነበረ ነው፡፡ ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ ግን ለመናገር እንኳን በሚያሳቅቅ የመከራ ድስት ውስጥ ከድኖ ሲቀቅል የኖረው የራሱን ህዝብ ነበር፡፡

“በአምባገነኑ ደርግ በመጨቆኑ አዝኜ ጫካ ገብቼ፣ ተራራ ቧጥጨ ታገልኩለት” የሚለውን ህዝብ መፈጠርን በሚያስረግም ግርፋት፣ ቁም-ስቅል፣ እስራት፣ ስደት እና መከራ ያሳለፈ ነፃ አውጭ ነኝ ባይ ህወሃት/ኢህዴግ ብቻ ነው፡፡ በኢህዴግ እስር ቤቶች የአጋንንት ሰራዊት እንኳን ተመካክረው ሊፈጥሩት የማይችሉት የጭካኔ ትዕይንት በክቡሩ የሰው ልጅ ላይ ተፈፅሟል፡፡ የሰው ልጅ ጀርባ በኤሌክትሪክ ገመድ ተተልትሏል፣ ሰው ከነነፍሱ እባብ ባለበት በጉርጓድ ውስጥ እንዲቀመጥ ተደርጓል፣ ሴት ወንዱ ተገዶ ተደፍሯል፡፡ ባጠቃላይ በነፃ አውጭ ነኝ ባዩ አሮጌው ኢህአዴግ ዘመን ስልጣን፣ ድንቁርና እና ብልግና ሲቆራኙ የሚፈጠረው ጥፋት ሁሉ ደርሷል፡፡የሰው ልጅ ክቡርነት ተረስቶ፣ ሰው ምናምንቴ፣ ስልጣን ደግሞ ክቡር ሆኖ ኖሯል፡፡

ከእስር ቤት ውጭ ያለው ዜጋም ቢሆን በመፍራት በመንቀጥቀጥ የኖረ፣ ካድሬ ደስ ባለው ቀን ያሰረበትን ዘመዱን መጠየቅ እንደ ሰማይ ርቆት፣ ጭቆናው ገላጋይ የሌለው መርገም መስሎት፣ እስር ቤት ባይገባም ቤቱን እስር ቤት አድርጎ በስነልቦና መረበሽ የሚማቅቅ ነበር፡፡ ኢህአዴግ ያሰረውን አስሮ ያላሰረውን የታሳሪ ቤተሰብ ስልጣኑ በፈቀደለት መጠን ሁሉ የሚያንገላታ፣ መንግስትነትን የማይመጥን እኩይ ማንነት ባለቤት ነበር፡፡ አረመኔው ኢህአዴግ በጭቃ ጅራፉ ገርፎ፣ ስሙን አክፍቶ ላሰረው ዜጋ ስንቅ እንዲያቀብል የሚፈቅደው ከቤተሰቡ በእድሜው የገፋውን ሰው መርጦ ነበር፡፡

ይሄኔ በልጆቻቸው መጦር የሚገባቸው፣ ለራሳቸው ያለ ድጋፍ መንቀሳቀስ የማይችሉ አቅመ ደካማ አዛውንት የታሳሪ ወላጆች ስንቅ ተሸክመው ከከተማ ዳር ባሉ እስርቤቶች ይንከራተታሉ፡፡ እነዚህ አዛውንቶች በዚህ መንከራተታቸው ጊዜ ሁሉ ከእብሪተኞቹ ነገስታት አልፈው እነዚህን እርኩሶች በላይዋ ላይ የሾመችውን ሃገር ጭምር የሚረግሙ ይመስለኛል! በህይወቴ የኢህአዴግ እርኩሰት ጎልቶ እንዲታየኝ ካደረጉኝ ምክንያቶች አንዱ ይህ አዛውንቶችን በማንከራተቱ ራሱን ጎበዝ አድርጎ የማየቱ ነገር ነው፡፡ በዚህ የተነሳ በዚህ ፓርቲ ውስጥ ተስማምቶ አመታትን ያስቆጠረ ሰው ሁሉ እስከዛሬ ይቀፈኛል፡፡ የኢህአዴግ ካድሬነት ከመሰረታዊ የሰውነት ባህሪ ጋር የሚጋጭ የሚመስለኝም ለዚህ ነው፡፡

መሰረታዊ የሰብዓዊነትን መርህን ችላ ብሎ ለስልጣን መደራደር ኢህአዴግን ኢህአዴግ ያደረግው ዋና ማንነቱ ነው፡፡ ተለወጥኩም ተለነጠቀጥኩም ቢል ኢህአዴግ ከዚህ ማንነቱ ፈቅ ነቅነቅ አይልም፡፡ተለወጥኩ ያለው የዶ/ር አብይ ኢህአዴግ በሰብዓዊ መብት ላይ አለቅጥ ሲያሾፍ የኖረውን ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሄርን አምባሳደር አድርጎ ሾሞ ሸልሞ አሳይቷል፡፡ አዲሱ ገ/እግዚብሄር ለሰብዓዊ መብት የቆመ ተቋምን እመራለሁ ብለው ወንበር ላይ ተቀምጠው በዛው መስሪያ ቤት ለሰብዓዊ መብት ጥሰት ሽፋን ሲሰጡ የነበሩ ተራ ዋሾ ሰው ነበሩ፡፡ ሰባ ሰባት ሽህ አማሮችን ስንት አመት ከኖሩበት ጉራፈርዳ ወረዳ በአንድ ሌሊት ነቅሎ ከህፃን እሰከ አዋቂ ዜጎችን ለመከራ የዳረገውን፣ በዚሁ ዝናው ባዕዳን እንኳን አምባሳደርነቱን አንቀበልም ያሉትን ሽፈራው ሽጉጤን ሃገር እየቀያየረ የሚሾመው አወዳሹ የበዛው የዶ/ር አብይ መንግስት ስለ ሰብዓዊነት ግድ ይለዋል ብሎ ምክንያታዊ ሰሚን ሊያሳምን የሚችል ሰው የለም፡፡ በሱማሌ ክልል ከአብዲ ኢሌ ጋር ያደረጉት እኩይ ስራ አልበቃ ብሏቸው አቶ ሙስጠፋን አላሰራ ያሉት አቶ አህመድ ሽዴ በተለይ በኋለኛው ሙከራቸው የተነሳ በፊት ላደረጉት በሱማሌ ክልል ለደረሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሁሉ ተጠየቂ ሊሆኑ ሲገባ አሁንም በንጉስ እልፍኝ ይሽሞነሞናሉ፡፡ወርቅነህ ገበየሁ የተባለውን የ1997 ባለዝና ገዳይ አስገዳይ እንደ ደህና ጌጥ በየምዕራቡ ሃገር ይዞ የሚዞሩት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፓርላማ ተገኝተው “እኛ ጥፍር ነቃዮች ህገ-ወጦች ነን” ያሉት ከአንጀት ነው ካንገት አጠያያቂ ነው፡፡

መቼም ለዶ/ር አብይ መንግስት ጠበቃው ብዙ ነውና እነዚህን በሰብዓዊ መብት ላይ ጉልህ ወንጀል የሰሩ ሰዎች መሾሙ ሃገር ለማረጋጋት ብሎ ነው፣ ሁሉም በአንዴ አይሆንም፣ አንዳንዱን ጥፋት መተው ነው የሚል አይጠፋም፡፡ በበኩሌ በሰው ልጅ ክቡርነት አጥብቄ የማምን ነኝና ገንዘብ ከዘረፈው ይልቅ የሰው ልጅን ሰብዓዊ መብት የረገጠው ሰው ይበልጥ ወንጀለኛ ሆኖ ይሰማኛል፡፡ ስለዚህ አንድ ቀን እንኳን ከተጠያቂነት ነፃ ሆኖ ሲንጎራደድ ማየት አልሻም፡፡ ሲቀጥል በኢህአዴግ እልፍኝ የሰብዓዊ መብት ነገር እጣ ፋንታ የሌለው ጉዳይ ስለሆነ መጠየቁ ቀርቶባቸው እነዚህ ሰዎች ከነክፉ ወንጀላቸው እንደማንኛወም ሰው እየወጡ እየገቡ መኖሩ አንሷቸው ስለ መሾማቸው ሿሚው አብይ ራሳቸው ከተራ ካድሬያዊ ሽኩቻ ባለፈ ሰው ፊት የሚያቀርቡት ምክንያት ያላቸው አይመስለኝም፡፡

ምናልባት ሃገራችን ካለችበት ክፉ የዘረኝነት ፖለቲካዊ አየር የተነሳ እነዚህን ሰዎች ተጠያቂ ማድረጉ የመጡበትን ዘር የሚያስቆጣ ሆኖ የሚያመጣው ችግር እንዳይኖር ተፈርቶ ነው የተሾሙት የሚል ክርክር ሊነሳ ይችላል፡፡ ይህ በነዚህ ሰዎች ሁኔታ የሚያስኬድ አይደለም፡፡ ህወሃት ከሌላው ፓርቲ በተለየ ሁኔታ ወከልኩት በሚለው ህዝብ ዘንድ ጥብቅና የሚቆምለት ስለሆነ በአቶ አዲሱ ገ/እግዚአብሄር ተጠያቂነት ምክንያት የሚነሳ ዘረኝነት ወለድ ጉም ጉም ባይጠፋም ሌሎቹ ሰዎች በስልጣን ዘመናቸው ባደረጉበት ማስመረር ምክንያት የወጡበት ህዝብ ራሱ ለፍርድ የሚፈልጋቸው ናቸው፡፡ የጄል ኡጋዴን መከራ ናፍቆት ለአህመድ ሽዴ ጥብቅና የሚቆም ሱማሌ አይገኝም፡፡ሽፈራው ሽጉጤም ቢሆን በወጣበት ህዝብ ዘንድ ወድቀህ ተነሳ የማይባል ስመ-ክፉ ሰው ነው፡፡የመለስ ዜናዊ የግድያ አጋፋሪው ወርቅነህ ገበየሁም ቢሆን ወዳጅነቱ ለዶ/ር አብይ ይሆናል እንጅ ለማንም ጎጥ ሰው አይደለም!

የሰብዓዊ መብትን ጉዳይ በተመለከተ ዶ/ር አብይም እንደማንኛውም ኢህአዴግ ቅም የማይላቸው ሰው እንደሆኑ ማሳያው ከላይ የተጠቀሰው ጉዳይ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቅስ የ1997 ዓም ምርጫን ተከትሎ በተደረገው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ በዳኛ ፍሬ ህይወት ሳሙኤል ሰብሳቢነት በተቋቋመ ገለልተኛ ኮሚሽን የተደረገውን ብዙ ዋጋ የተከፈለበት ሪፖርት ተቀብለው በሃሰተኛው ቦታ እንዲተኩ በተደጋጋሚ ከኮሚሽኑ አባላት የሚቀርብላቸውን ጉትጎታ ችላ ማለታቸው ነው፡፡ እነዚህ የኮሚሽኑ አባላት አሁን የለውጥ ሃይል ነኝ የሚለው የነዶ/ር አብይ ቡድን አንገቱን ደፍቶ፣ ከግፈኛው መለስ ዜናዊ ጋር አብሮ፣ ግፍን ሁሉ አሜን አሜን በሚልበት በዛ አስፈሪ ዘመን አንገታቸው ላይ የተሳለ ቢለዋ ሊያርፍ እንደሚችል እያወቁ ከእውነት ጋር ብቻ ያበሩ፣ በሞራል ልዕልና የለውጥ ሃይል የተባለውን ጭምር የሚያስከነዱ ሰዎች ናቸው፡፡

እነዚህ ያለጊዜው ጭምር የፀኑ ሰዎች የኢህአዴግ ካድሬ ሁሉ ምስል ቀርፆ ሊያመልከው የደረሰው መለስ ዜናዊ በመንበሩ ቁጭ ብሎ እያለ ነው ነፍሳቸውን ሸጠው የህዝብን አደራ ብቻ አንግበው ከሞት ጋር የሚፋጠጡበትን አስፈሪ መንገድ የተጓዙት፡፡ በዚህ ጉዟቸው ውስጥ የተረጋጋው ኑሯቸው ተናግቷል፣ ለዱብዳ ስደት በመዳረጋቸው ቤተሰባቸው ተበትኗል፣ ህይወታቸው ተመሰቃቅሏል፡፡ለህዝብ ሲሉ ይህን ሁሉ ስላደረጉ ሊመሰገኑ ሲገባ ሊሞቱለት የቆረጡትን፣ ብዙ የለፉበትን ነገር ተራ ጥቆማ አድርጎ ማቃለል ራስን ማስገመት ነው፡፡በርግጥ በሃሰት ፖለቲካ፣ በጌታ ፈቃድ እያደረ የኖረ የኢህአዴግ ባለስልጣን ለእውነት ሲባል የሚከፈልን መሰዕዋትነት ለመረዳት እና ተገቢውን ክብር ለመስጠት ሊቸግረው ይችላል፡፡ ይህን መሰረታዊ ኢህአዴጋዊ ባህሪ እንደተሸከሙ የለውጥ መሪ ነኝ ማለቱ ግን የሚገጥም ነገር አይደለም፡፡

የኮሚሽኑ አባላት መለስ ዜናዊ ያቀረበላቸውን፣ የኢህአዴግ ካድሬ የእለት ተዕለት ኑሮው አካል የሆነውን የሃሰት ግብዣ እምቢ ብለው ከሃገር የወጡበት መንገድ እጅግ አስገራሚ ነው፡፡ ነገሩ የሰዎቹን የእውነት ሰውነት የሚያሳይ፣ ሌላ ሃገር ቢሆን ትልቅ ሽልማት የሚያሰጣቸ፣ ለትውልድ ትምህርት የሚሆን ስራ ነው፡፡ የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ዳኛ ፍሬ ህይወት በተበደለው ህዝባቸው ላይ ሌላ ሃሰት ጨምሮ በህዝብ ቁስል እንጨት ላለመስደድ ሲሉ በቦሌ በኩል የወጡበትን መንገድ ለኢሳት ቀርበው ሲያስረዱ በበኩሌ ነገሩ ማለፉን ሁሉ ረስቼ በትልቅ ጭንቀት ተወጥሬ ነበር ያዳመጥኳቸው፡፡በዛች ቅፅበት ያቀዱት አንዱ ነገር ውልፊት ብሎ በመንግስት ውስጥ እጅ ቢወድቁ ሊደርስባቸው የሚችልውን ነገር ማሰቡ የሰውየውን የፍትህ ሰውነት ለመረዳት ያግዛል፡፡ ምድረ ካድሬ እንደ አምላኩ የሚያረግድለትን፣ በቀለኛውን መለስ ዜናዊን እምቢ የማለታቸው ድፍረት ሳያንስ ኮሚሽኑ በማጣራቱ ወቅት በጥንቃቄ ያደራጃቸውን መረጃዎች ሁሉ ሰብስበው ይዘው ለመውጣት በሚገርም ድፍረት ማሰባቸው እና ማሳካታቸው ሁሌ የሚገርመኝ ነገር ነው፡፡ ከዚህ የምንረዳው ለዳኛ ፍሬህይወት ፍትህ በደማቸው ውስጥ የሚዞር ነገር እንጅ ለእንጀራ ሲሉ ብቻ የያዙት ጉዳይ እንዳልሆነ ነው፡፡ እስከ ዛሬ ለፍትህ የሚሞግቱት ሌሎቹ የኮሚሽኑ አባላት እነ አቶ ምትኩ ተሾመ፣ ዳኛ ወ/ሚካኤል መሸሻ፣ አባ ቲዎፍሊዎስ ሁሉ የህዝብን አደራ ከመብላት ራሳቸውን ለመስዕዋት ያቀረቡ ድንቅ ኢትዮጵያዊያን ናቸው፡፡

በጣም የሚያሳዝነው እና የሚገርመው ተለውጫለሁ የሚለው መንግስት እነዚህን ሰዎች በክብር ጠርቶ ሪፖርታቸውን እንዲያቀርቡ ማድረግ ሲገባው በህይወታቸው የተደራደሩበትን ሪፖርት እያቃለለ መሆኑ ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ለዶ/ር አብይ መንግስት ከየአቅጣጫው እየወረደ ያለው የበዛ የውዳሴው ድቤ አቅሉን እንዲስት እንዳደረገው ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለማም አይበጅም! ይብስ የሚገርመው ደግሞ ለወትሮው ለፍትህ እቆማለሁ የሚለው ተቃዋሚ ሃይልም ሆነ ህወሃትን ለማብጠልጠል ምክንያት የማይፈልገው ጋዜጠኛ ሁሉ ስለዚህ ጉዳይ ትንፍሽ አለማለቱ ነው፡፡ ጭራሽ ለፍትህ እሟገታለሁ ሲል የኖረው ጋዜጠኛ እና ፖለቲከኛ የዶ/ር አብይ መንግስት በስራው ሁሉ ትክክል ነው እንደ ማለት የሚሞክረው የፖለቲካ አዝማሪነት ውስጥ እየገባ ነው፡፡ ይህ አካሄድ ስለማያዋጣ የአጣሪ ኮሚሽኑን ተገቢ ጥያቄ ዳር ለማድረስ ሰብዓዊነት ይሰማኛል ባይ ሁሉ በሃቅ ላይ ፊቱን ባዞሮው የዶ/ር አብይ መንግስት ላይ ጫና ማሳደር አለበት፡፡ ይህን ስለተባለ የአብይ መንግስት አይሟሟም!

አሁን የለውጥ ሃይል የሚባለው የኢህአዴግ ቡድን በ1997 ለደረሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ቢያንስ በዝምታ ድጋፍ የሰጠ ነው፡፡ በአንፃሩ ዛሬ ስለ እውነት የሚማፀኑት የኮሚሽኑ አባላት በህዝብ ላይ የደረሰውን በደል ለማጋለጥ በነፍሳቸው የተደራደሩ ሰዎች መሆናቸው ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች የህዝብን ትግል ተተግነው የለውጥ አራማጅ ነን ያሉትን የዛሬዎችን ገዥዎች ሳይቀር የሚልቅ የሞራል ልዕልና ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡በመሆኑም ዛሬ ስልጣን ላይ የወጣው ቡድን የኮሚሽኑን ሪፖርት በመቀበል የትናንት ጥፋቱን የማረም ግዴታ አለበት፡፡ ካልሆነ ስለትናንቱ መጠየቅም እንደሚኖር ማሰብ ደግ ነው፡፡ የኮሚሽኑ አባላት የተመሰከረለት ለእውነት የመቆም ፅናት ደግሞ ጉዳዩን የትም ድረስ የመውሰድ ብርታት እንዳለው ለማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ነገሩ ተጓትቶ ባዕዳን ደጃፍ ከመድረሱ በፊት የለውጥ አመራር ነኝ ባዩ የሃገራችን መንግስት ህይወት የተገበረበትን፣ ቤተሰብ የተበተነበተን ትልቅ ጉዳይ ማቃለሉን ትቶ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ባይወድም ግዴታው እንደሆነ ማወቅ አለበት፡፡

የምንግዴው ኢህአዴግ ስንጣቂ መሆኑ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ብልጭ የሚለው የለውጥ አመራር የኮሚሽኑን ሪፖርት ተቀብሎ በሃሰተኛው ቦታ ለመተካት የተቸገረው ለምንድን ነው? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ የዚህ ዋነኛው ምክንያት ሃሰት ላይ ተመቻችቶ ተኝቶ ለእንቅልፍ ያለመቸገር ለቆ የማይለቅ ኢህአዴጋዊ የክህደት ተፈጥሮው ነው፡፡በመቀጠል የዶ/ር አብይ መንግስት በአደባባይ ከሚያወራው የለውጥ ማንነት ጋር ልዩነት ያለው ውስጣዊ ማንነት ስላለው ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይህ ደግሞ ትርጉሙ አስመሳይነት ነው፡፡ በሰው ደም ላይ ተመቻችቶ ተቀምጦ የስልጣንን ማረፊያ ማመቻቸት ተቀየርን ብለውም እንኳን የኢህአዴ ካድሬዎችን የማይለቃቸው ልዩ ተፈጥሮ ነው፡፡ ይህ ክፉ አመል ነው የሰብዓዊነትን ጉዳይ ችላ የሚያስብላቸው፡፡በተቀረ ሰዎች ለፍተው ደክመው፣ መለስ ዜናዊ ከሚባል ጨካኝ አምባገነን ጋር አባሮሽ እየተጫወቱ ያጣሩትን የህዝብ እውነት ማድበስበስ ያከስር ይሆናል እንጅ የፖለቲካ ትርፍ አያመጣም፡፡ አሁን በዶ/ር አብይ አመራር የተያዘው እውነትን ማድበስ ሁነኛ ምክንያቱ እንደ ወርቅነህ ገበየሁ ያሉ የ1997ቱ ግድያ መሪ ተዋናዮችን (የአሁን ዘመን ደግሞ የለውጥ አመራር አጋፋሪዎች) ተጠያቂ ላለማድረግ ነው፡፡ በደሉን ረስቶ፣ ጥፋትን ሁሉ ይቅር ብሎ ወንበር ላይ ላስቀመጠ ህዝብ ከመቆም እና ለወንጀለኛ ባለስልጣናት ሽፋን ከመስጠት የሚያዋጣው የቱ እንደሆነ ውሎ አድሮ ይለያል!

Tuesday, January 15, 2019

በማንነት ጥያቄ እና በብሶት ትርክት የተሞላው የፖለቲካ አዙሪት!



ሰዎች ብሶታቸውን ለመወጣት ወይም የጎደለ ጥቅማቸውን ለማሳካት ሊደራጁ እና ሊታገሉ ይችላሉ። መብትም ነው። የመደራጀት መብት አንዱ እና ከጀርባው ያለው አመክንዮም ሰዎች በተናጠል ሊያሳኩት ያልቻሉትን ጉዳይ ወይም የጎደለባቸውን ጥቅም ወይም ሊያገኙ የሚመኙትን ወይም ያገኙትን ይዞ ለማቆየት ሲሉ ተመሳሳይ ፍላጎት ካላቸው ሰዎች ጋር ህብር ይፈጥራሉ። “ልጥ ቢያብር አንበሳ ያስር” እንደሚባለው ሁሉ በጋራ በመቆም ህልማቸውን ያሳካሉ፣ ጥማታቸውን ያረካሉ፣ የጎደለባቸውን ይሞላሉ፣ ካሰቡት ለመድረስም በተሻለ አቅም ይተጋሉ። መደራጀት ከዚህ ያለፈ ፋይዳ የለውም። ሰዎች በመደራጀት ሊያገኙት የሚችሉትን ዋና ጥቅም እና ግብ በግላቸው ሊያሳኩ የሚችሉ ቢሆን ኖሮ እድር፣ እቁብ፣ ጽዋ ማህበር፣ የኃይማኖት ድርጅት፣ የፖለቲካ ድርጅት፣ የሙያ ማህበር፣ የበጎ አድራጎት ማህበር፣ ወዘተ የሚባሉ የማህበር ኮልኮሌዎች አይኖሩም ነበር።

የሰው ልጁ በተፈጥሮም ግለኛ ነው። ሁሉን ነገር ለራሱ እና በራዙ ዙሪያ ነው የሚያስበው። እኔ ብሉ ይጀምራል ከዛም እኛ ብሎ ይጨርሳል። በእኛ ውስጥም እኔ አለ። እራሱን የሁሉም ነገር ስበት ማዕከል አድርጎ ነው የሚያስበው። እኔ እና እኛ በሚለው ውስጥ እራሱን፣ ቤተሰቡን፣ ልጆቹን፣ ካገባም የትዳር አጋሩን፣ ዘመድ አዝማዱን፣ የዘር ሃረግ፣ ጎሳ፣ የትውልድ አካባቢ፣ አገር እያለ እንደ ጭንቅላቱ ስፋት አለም አቀፍ የእኔ እና የእኛ መገለጫ ማዕከሎች ይፈጥራል። የአንድ ሰው የእኔ እና እኛ ክብ ስብስቦች እንደ ሰውየው የእውቀት እና የማገናዘብ ችሎታ ይጠባል፤ ይሰፋልም።

የአንዳንድ ሰው የእኔ እና የእኛ ማዕከል ከራሱ ወይም ከቤተሰቡ ወይም በዘር ሃረግ ወይም በቋንቋ ወይም በጎሳ ከሚመሳሰሉት ጋር ብቻ ይወሰናል። ይህ አይነቱ ሰው እርምጃው ሁሉ በእነዚህ የእኔነት ክቦች የታጠረ ነው። ሲደራጅ፣ ሲበላም፣ ሲሰራም፣ ጥቅሙን ሲፈልግም፣ ሲያሰላም የሚሰባሰበው በእነዚህ ክቦች ዙሪያ ነው። አንዳንዱ ደግሞ ለእናት እና ለአባቱ አንድ ሆኖ ተፈጥሮም የሰው ዘር ሁሉ ወንድሙ፣ እህቱ፣ ዘመዱ፣ የዘር ሃረጉ ይሆንና ከማንም ሰው ጋር ጸኦታ፣ ቀለም፣ እድሜ፣ የትውልድ ስፍራ ወይም የሃብት ምንጭ ሳይወስነው ይዛመዳል፣ ይቧደናል፣ አብሮ ይኖራል፣ አብሮ ይሠራል፣ አብሮ ይበላል፣ አብሮ መከራን ይጋፈጣል፣ አብሮ ያቅዳል፣ የራሱ ብቻ ሳይሆን የሌሎች ሰዎች ጉዳይ ሁሉ ያሳስበዋል፣ የራሱም ጉዳይ የሌሎች ጉዳይ እንደሆነ ያህል ይሰማዋል።

ወደ ተነሳሁበት ዋና ርዕስ ልመለስና የብሶት ፖለቲካ ሁል ጊዜ በክቦች የታጠረ ነው። አንድ ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸው ወይም አንድ የጋራ የሚያዛምድ የጥቅም ትስስር ያላቸው ሰዎች ጎደለብን ያሉትን ጉዳይ የፖለቲካ መዘውሩን በመያዝ ለመሙላት፣ የተነጠቁትን ለማስመለስ፣ የተመኙትን ለማሳካት በፖለቲካ ድርጅት ተቧድነው ወደ ትግል ሊገቡ ይችላሉ። ይህ አይነቱ መቧደን በራሱ ምንም ችግር የለበትም። በፖለቲካ የመቧደን ፋይዳውም ከዚህ የዘለለ ላይሆን ይችላል። ችግር የሚፈጠረው የተቧደንንበት የፖለቲካ ክብ ስፋት እና ጥበት፤ አቃፊነት እና አግላይነት ላይ ነው። እነ ማንን አቅፎ እነ ማንን ያገላል፣ ምን ያህል አሳታፊ ነው፣ ምን ያህል አግላይ ነው የሚሉት ነጥቦች የፖለቲካ ክቡን የፈጠሩት ሰዎችን ማንነት፣ ባህሪ፣ የዕውቀት ደረጃ እና ስነ ልቦናቸውን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

አቃፊ የሆነው የፖለቲካ ክብ በጠበበ ቁጥር የተሳታፊው መጠን ይጠባል። በውስጡ የሚሳተፉም ሆኑ የሚታቀፉ ሰዎች ቁጥር የዛኑ ያህሉ ውሱን ይሆናል። የአቃፊነቱ መለኪያው አንድ የፖለቲካ ጽንሰ ሃሳብ ወይም ርዮተ አለም ሲሆን እና ከማንነት መገለጫዎች ከሆኑት በአንዱ ላይ የተመሰረተ ሲሆን እንዲሁ አቃፊነቱም ሆነ አግላይነቱ የተለያየ ይሆናል። የሃሳብ ወይም የአመለካከት ማዕቀፍ ሲሆን በክቡ ውስጥ ለመታቀፍ መስፈርቱ ያንን ገዢ የሆነ ሃሳብ የራስ ማድረግ ብቻ ነው። ስለዚህ ያንን ሃሳብ የሚደግፍ ማንኛውም ሰው ሌሎች የሕግ መስፈርቶች እንደተጠቡቁ ሆነው በተዋቀረው የፖለቲካ ክብ ውስጥ ሊታቀፍ ይችላል።



በሃሳብ ላይ የተሰመሩ የፖለቲካ ማቀንቀኛ ክቦች ሰፊ እና አቃፊዎች ናቸው። መገለልም ሆን መታቀፍ ለእያንዳንዱ ሰው የተተዉ ምርጫዎች ናቸው። በፖለቲካ አደረጃጀት ደረጃ ትልቁ ክብም ይኼው በሃሳብ ላይ ወይም በአመለካከት ላይ የሚዋቀረው የፖለቲካ ማዕቀፍ ነው። በምሳሌ ለማስረዳት ዲሞክራት ወይም ሪፐብሊካን፣ ሶሻሊስት ወይም ሊብራል የሚሉት ማዕቀፎች የአመለካከት መሰረቶች ናቸው።

ከላይ ከተገለጹት ማዕቀፎች ጠበብ ሲል ደግሞ፤ የሠራተኖች ፓርቲ፣ የክርስቲያን ዲሞክራት ፓርቲ፣ የአርሶ አደሮች፣ የሴቶች፣ የገጠር ነዋሪዎች፣ የከተማ እያለ ይቀጥላል። እነዚህ ደግሞ በተወሰነ ደረጃ በባህሪያቸው አግላይ ቢሆኑም ሰፊ የሆነ የህብረተሰብ ክፍልን የሚያቅፉ ናቸው። በውስጣቸው በብዙ ነገሮች የተለያየ መገለጫ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ያቅፋሉ። ከዚህ ወረድ ሲል ያለው አደረጃጀት ደግሞ የመሬት አከላለልን ወይም አንድ በተወሰነ ቦታ ላይ የተማከለ አደረጃጀት ነው። እንዲህ እያለ ክቡ ወደ ታች በወረደ መጠን እየጠበበ ይሄዳል። ብሔርን፣ ቋንቋን፣ ዘርን፣ ጎሳን፣ ጎጥን፣ መንደርን እያማከለ ይሄዳል።

ብሔርን፣ ቋንቋን፣ ዘርን፣ ጎሳን፣ ጎጥን እያማከለ የሚወርደው የፖለቲካ አደረጃጀት ክብ የመደራጃ መሰረቱም ሆነ መስፈርቱ ሃሳብ ወይም የፖለቲካ እርዮተ አለም አይደለም። እነዚህን የማንነት መገለጫዎች ማሟላት ብቻ በቂ ነው። የአንድ ብሄር አባል መሆን በዛ ብሔር ስም በሚዋቀረው ክብ ውስጥ ለመታቀፍ በቂ ነው። የአንድ ጎሣ አባል መሆን በጎሣ ደረጃ ለሚዋቀረው ክብ በቂ መመዘና ነው። በዛኑ መጠን ክቡ የተዋቀረበት ብሄር ወይም ጎሣ ወይም ዘር አባል ያልሆነ ሰው በእነዚህ ክቦች ውስጥ ታቃፊ ሊሆን አይችልም። ስለዚህ በጥበትም ይሁን በአግላይነት የመጨረሻውን ደረጃ የሚይዙት እነዚህ የማንነት መገለጫ በሆኑት መስፈርቶች ዙሪያ የሚዋቀሩ ክቦች ናቸው።

ክቦቹ በጠበቡ ቁጥር ከትልቁ የሃሳብ እና የፖለቲካ እርዮተ አለም ምልከታዎች እየራቅን እንሄዳለን። ሃሳብ እየመነመነ ማንነት እየጠበደለ ይሄዳል። ሃሳብ የሚመነምንበት ቦታ ላይ ብዙ መመራመር፣ ቡዙ ማወቅና መማር፣ ብዙ መፈላሰፍ፣ ብዙ ለእውቀት እና አዲስ የፖለቲካ አመለካከት ለማፍለቅም ሆነ ለመቀበል የሚሆን ቦታ የለም። እነኚህ የማንነት መገለጫዎች ጠባቡ ክብ ስለሚሞሉት የዛ ማንነት ባለበት መሆን ብቻውን የክቡ እድገት መገለጫ ነው። እንዲህ ያሉ በማንነት ላይ የተዋቀሩ የፖለቲካ ክቦች የጥንካሬያቸው መገለጫ የፖለቲካ ሃሳባቸው በሳይንሳዊ መርምር መደገፍ ወይም የረቀቀ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማፍለቅ መቻል ወይም በአዳዲስ የፖለቲካ ሃሳቦች መምጠቅ አይደለም። ትልቁ ጥንካሬያቸው ከኋላ የሚያሰልፉት ሰልፈኛ እርዝመት ወይም ብዛት እና ማንነት ነው። ስንት አማራ፣ ስንት ኦሮሞ፣ ስንት ትግሬ፣ ስንት ጉራጌ፣ ስንት ወላይታ፣ ስንት ከንባታ፣ ስንት አፋር፣ ስንት ጋሙ፣ ስንት ሲዳማ፣ ወዘተ ። ለእነዚህ አይነት አደረጃጀቶች አጠገባቸው ካለው እና ተመሳሳይ ብሶት ካለበት የሌላ ብሔር ተወላጅ ይልቅ በእርቁ ያለው እና የእኔ ብሄር አባል የሚልት ነገር ግን የማያውቁት ሰው ከፍ ያለ ዋጋ አለው።

እነዚህ ክቦች የተፈጠሩት በማንነት መገለጫ ልክ ስለሆነ አሻግረው በሌላ የማንነት ክብ ውስጥ ያሉትን አያዩም። ካዩም በፉክክር መንፈስ እንጂ ክቦቹን በማስፋት ወደ አንድ ክብ ለመጠቃለል አይሆንም። በማንነት መገለጫዎች የሚዋቀሩት የፖለቲካ ማዕቀፎች ከጥንስስ ሃሳባቸው አንስቶ የድርጅት ቅርጽ ይዘው አደባባይ የሚወጡት የብሶት ክምር ይዘው ውንጂ የፖለቲካ ማቀንቀኛ ንድፈ ሃሳብ ወይም የተለየ እርዮት አለም አይደለም። በብሶት ይጠነሰሳስሉ፣ በብሶቱ ያድጋሉ፣ በብሶት ጡዘት ይጎለምሳሉ፣ በብሶት ያረጃሉ፣ ከነብሶታቸ ግን አይከስሙም ሌላ ሆድ የባሰው ጨቅላ ተክተው ያልፋሉ። የብሶት ፖለቲካ ዋና ግቡ በክቡ ውስጥ ያሉጥን ሰዎች መሰረታዊ የሆኑ ችግሮችን መፍታት እና ወድ የባሰው ሌላ ትውልድ እንዳይፈጠር ምንጩን መድፈን ሲሆን ግባቸውን ካሳኩ በኋላ አንድም ይከስማሉ አለያም ክቡን አስፍተው ወደ ሃሳቦ ጎዳና ይመጡና በእርዮት አለም ላይ የሚያጠነጥ ፖለቲካ ያራምዳሉ።

የብሶት ድርጅቶች አላማቸው ሆድ በባሰው ሕዝም ስም መነገድ እና የሥልጣን ጥማታቸውን ማርካት ከሆነ ግን እራሳቸውም ብሶት አፍላቂ ይሆናሉ። ቦሶት እንዳይነጥፍ እና ህልውናቸውም አብሮ እንዳያከትም የቆየ ቑጽል መጎድፈር ብቻ ሳይሆን አዳዲስ ቁስልም የምስፍጠር አቅም እና ችሎታ የዘው ይወጣሉ። ብሶት ከመታገያነት አልፎም የህልውና ማስጠበቂያ መሣሪያ ይሆናል።

የብሔር ድርጅቶች ሁሌም የሚያነሱት የመሟገቻ ሃሳባቸው እንታገልለታለን የሚሉት እና በክባቸው ውስጥ በሃሳብም ቢሆን የከተቱት የህብረተሰብ ክፍል ያጣቸው፣ ያልተከበሩለት እና የተነፈጉት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ እና ሌሎች ጥቅሞች አሉ የሚል ነው። እነዚህን ጥቅሞች የፖለቲካ ሥልጣኑን በመያዝ እናስከብራለን ባዮች ናቸው። በእርግጥ የፖለቲካ ሥልጣን የፈለጉት ጥቅም ለማስጠበቂያ የሚረዳ መሳሪያ ነው። ሰዎች በማንነታችን የተነሳ የተነፈጉትን መብት እና ጥቅም ለማስጠበቅ በተለያዩ መልኩ ሊደራጁ እና ሊታገሉ ይችላሉ። ለሥልጣን መታገል ግን ሌላ ገጽታ አለው።

ሕውሃትን ጨምሮ ዛሬ በሥልጣን ላይ ያሉት ብዙዎች ድርጅቶች ለአሥርት አመታት የታገሉት በዚህ መነሻ ሃሳብ ነው። ስልጣን ሲይዙ ግን ታገልንለት የሚሉት ሕዝብ ትዝ አላላቸውም። የታገሉበትን አሥርት አመታት ትተን ሥልጣን ላይ በወጡ ከሃያ ሰባት አመታት ቆይታ ብኋላም እንታገልለታለን ያሉት ህዝም በብሶት ላይ ብሶት ተደርቶበት መገኘቱ የብሶት ፖለቲካን ባህሪ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ብሶት የወለዳቸው የዛሬዎቹ ገዢዎች ሥልጣን ሲይዙ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሶት ቢለካ ምናልባት ወገቡ ድረስ ውጦት ይሆናል። ከሃያ ሰባት አመት የብሶት ፖለቲካ ምሪት በኋላ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሶት እንደተራራ ገዝፎ እና ተቆልሎ አንዱ ብሔር ሌላውን እንዳያይ ጋርዶታል።

ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ብሶት ያልዋጠው የህብረተሰብ ክፍል የለም። ሁሉም ብሶተኛ ነው። ኢትዮጵያ በብዙ የብሶት ተራራዎች ተውጣለች። የኃይማኖት ብሶት፣ የብሔር ብሶት፣ የክልል ብሶት፣ የማንነት ብሶት፣ ብሶት በብሶ ሆነናል። ሁሉም በደጃፉ እና በተቧደነበት ክብ ውስጥ በተቆለለው ብሶት ተውጧል። ብሄረተኝነት እና ብሶት ሲገናኙ ደግሞ ቤንዚን እና እሳት እንደማለት ነው። በብሶት ቁልላቸው የሚፎካከሩት የብሄር ብሶት ፖለቲከኞች ጡዘቱን ሰለሚያከሩት አንዱ ብሶተኛ ሌላውን አያዳምጥም። ከባልሽ ባሌ አይነት፤ ከአንተ ብሶት የኔ ብሶት ይበልጣል እያለ ሁሉም ስለሚጮኽ አድማጭ አይኖርም። ብንደማመጥ ሁላችንም ተመሳሳይ ብሶት የዋጠን የመጥፎ ሥርዓቶች ሰለባዎች ነን።

የብሄር ብሶት አቀንቃኝ ድርጅቶች እድሜ ሊኖራቸው የሚችለው ሦስት መሰረታዊ ነገሮችን መነሻ ስለሚያደርጉ ነው። አንደኛው በእርግጥ በዛ አገር ታሪክ ውስጥ በአንድ ዘር ላይ ወይም በአንድ ብሔር ላይ ብቻ ወይም በአንድ የተለየ የማንነት መገለጫ ባለው የህብረተሰብ ክፍል ላይ ብቻ ያነጣጠረ እና አግላይ የነበረ መንግስታዊ አስተዳደር ከነበረ ነው። ሁለተኛው ደግሞ ይህ አይነቱ በአንድ የህብረተሰብ ክፍል ማንነት ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ወይም በደል ዛሬም ቀጥሏል ወይ የሚለው ነው። ሦስተኛው ደግሞ በማህበረሰቡ ውስጥ በማንነት መድልዎ የተነሳ የተፈጠሩትን ችግሮች፣ የምጣኔ ሃብት እና ሌሎች የጥቅሞ መበላለጦችን ያስከተሉት አሰራሮች እና ጥቃቶች ወደፊትም ይቀጥላሉ የሚል ስጋት ሲኖር ነው።

ከአርባ አመት በላይ በዚህ ፖለቲካ ያረጁ እና ያፈጁ ድርጅቶች ዛሬም በዛው አደርጃጀታቸው በቀጠሉበት እና አዳዲስ ግልገል ብሔረተኛ ድርጅቶች እየፈለቁ ባለበት አገር ከብሶት እና ከብሄር ተኮር ፖለቲካ ወደ ሃሳብ ፖለቲካ የሚደረገው ሽግግር እንዲህ ቀላል አይሆንም። አሁን የታየችውን የተስፋ ጭላንጭል ያዩ ብዙዎች የዘር ፖለቲካ በማግስቱ ተጠራርጎ ጠፍቶ ለማየት መመኘታቸው ትንሽ የዋህነት ይመስለኛል።

የብሔር ፖለቲካ ከኢትዮጵያ እንዲህ በአጭር ጊዜ እና በቀላሉ ይጠፋል የሚል እምነት የለኝም። ለዚህም ሁለት ምክንያቶችን ጠቅሼ ሃሳቤን ልቋጭ። አንደኛው የዘር ፖለቲካው የመሸገባቸው የብሶት ተራራዎች እንኳን ሊከስሙ ጭራሽ እየገዘፉ አገራዊ እይታችንንም እየጋረደን ነው። እንዲህ በቀላሉም የሚናዱ አይመስለኝም። ሊናዱ የሚችሉት ብሶቶቹን በአግባቡ ሊመልስ የሚችል እና ምንጫቸውንም የሚያነጥፍ ሥርዓተ መንግሥት በአግባቡ ሲዋቀር እና እነዚህ የሕዝብ ብሶቶች በአግባቡ ተጠንተው በጥንቃቄ በተቀረጹ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች ምላሽ ሲያገኙ፤ በተጨማሪም ተቋማዊ ዋስትና ሲኖራቸው ነው። ሁለተኛው ግን የብሄር ፖለቲካ አቀንቃኞችም ሆን የብሔር ስታቴጂስቶች ከታሪክ የሚቆፍሩት የብሶት ቁስል አልበቃ ሲላቸው አዳዲስ ብሶቶች እንዲፈበረኩ የሚያደርቱግን እኩይ እንቅስቃሴ ማቆም ሲችሉ ነው። ብሶት እና ሕዝብን በማንነቴ ተጠቅቻለው ብሎ እንዲያስብ የሚያደርጉት ነገሮች የእዝጌር ቁጣ ወይም ከሰማይ የሚወርዱ ነገሮች አይደሉም። አብዛኛዎች በፖለቲከኞች እኩይ እሳቤ እና ኃላፊነት የጎደለው እርምጃ እና የሃሰት ትርክቶች የሚፈበረኩ ናቸው።

ሕዝብን በዘር ለማቧደን በመጀመሪያ በዘሬ ተበድያለሁ ብሎ እንዲያስብ ማድረግን ይጠይቃል። ይህን ደግሞ አንድም በትክክት የተፈጠሩ በደሎችን ደጋግሞ በመንገር ሕዝቡን የብሄር ብሶተኛ ማድረግ ይቻላል። ሁለተኛው ደግሞ በታሪክ የተፈጠሩትን በደሎች ሁሉ ችላ ብሎ ወይም በሁሉም ላይ የደረሰ ነው ብሎ አስቦ የብሄረተኝነት ከረጢት ውስጥ አልገባም ያለውን ሰው የጥቃት ሰለባ እንዲሆን ማድረግ ነው። ከመኖሪያ ቦታው ከሌሎች ነጥሎ ማፈናቀል፣ ከትምህርት ገበታው ማባረር፣ ማዋከብ እና ማሳደድ አንዱ ስልት ነው። በማንነቱ ላይ የተነጣጠሩ ጥቃቶች እንደ ክረምት ዝናብ ዛሬም ነገም እየመጣ መጠለያ ሲያሳጣው ያኔ የዘር ጥቃት ምን እንደሆነ ይገባዋል። ያኔ በዘሩ ይደራጃል። ያኔ እራሱን ከጥቃት የተከላከለ ይመስለውና ወደ መከላከል ይገባል። ያኔ በተፈበረከ ብሶት ወደ ብሔረተኝነት ይገባል። የሚፈለገውም ይሄው ነው።

እንደ ኢትዮጵያ ባለ አገር የብሔር ፖለቲካን ማሳካት የሚቻለው ሁሉንም ብሔረተኛ ማድረግ ሲቻል ብቻ ነው። አንድ ብሔር በብሔሩ ተደራጅቶ ሌሎች ህብረ ብሔራዊ ሆነው ቢቀጥሉ ለብሔረተኛው ድርጅት ኪሳራ ነው። አያተርፍም። እሱ ወደ ሌሎቹ መንደር ባይሔድም ህብረ ብሔር ድርጅቶቹ ግን አገር አቀፍ እንቅስቃሴ ስለሚያደርጉ ወደ እሱ መንደር ይመጣሉ። ያኔ ይዋጣል። ሁሉም ብሔረተኛ ከሆነ ግን ውድድሩ በየብሔሩ ስለሆነ አንዱ የሌላው ወዳጅ ባይሆንም ስጋት አይሆንም። የኦሮሞ ድርጅቶች ኦሮሚያን፤ የአማራ ድርጅቶች አማራ ክልልን፤ የትግራዩ ትግራይን፤ የአፋሩ አፋርን ለማስተዳደር ስለሆነ ህልማቸው ሲሻቸው በፌደሬሽን አብረው ይኖራሉ። ሲሻቸው ሁሉም አገር ይሆናሉ። የመጣንበት የሃያ ሰባት አመት ጉዞ እውነታው ይሄው ነበር።

እነዚህን ጥያቄዎች ለእርሶ ለተው እና ጽሁፌን ልቋጭ፤

በቀጣይ ወዴት እናመራ ይሆን?
እርሶስ እራስዎን በየትኛው ክብ ውስጥ ነው ያስቀመጡት?
በብሶት ወይስ በሃሳብ ፖለቲካ መቀጠል የሚፈልጉት?

በቸር እንሰንብት!

Wednesday, December 12, 2018

የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰላም ሲዘምር ህወሓቶች ለጦርነት ይፎክራሉ! ለምን?

የህወሓት አባላትና አመራሮች የሚያሳዩት ባህሪና የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለብዙዎች ግልጽ አይደለም። ብዙሃኑ የህብረተሰብ ክፍል የተቀበለውን ለውጥ እነሱ ይቃወሙታል። በሀገራችን የተጀመረው ለውጥ በብዙሃኑ ዘንድ ድጋፍና ተቀባይነት ሲያገኝ ህወሓቶች ግን ሲያጣጥሉትና ሲቃወሙት ይስተዋላል። ብዘሃኑ የህብረተሰብ ክፍል ስለ ስላም ሲናገር እነሱ ስለ ጦርነት ይዘምራሉ። የህወሓት አባላትና ደጋፊዎች ለውጡን የሚቃወሙበት መሰረታዊ ምክንያት ምንድነው? በእርግጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ሌሎች የፖለቲካ ቡድኖች ለየት (የተለየ) የሚያደርጋቸው ነገር አለ?

የችግሩ መሰረታዊ መንስዔ ያለው የህወሓት ዓላማና ግብ የአንድ ወገን የበላይነትን ማረጋገጥ መሆኑ ላይ ነው። ህወሓት እንደ ግለሰብ የድርጅቱን አመራሮች፣ እንደ ቡድን የድርጅቱን አባላት፣ እንደ ማህብረሰብ ደግሞ የትግራይን ህዝብ የበላይነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ የተመሰረተ ነው። ይህ ከደደቢት እስከ ቤተ-መንግስት፣ ከአዲስ አበባ እስከ መቀሌ ድረስ ያለና የነበረ የድርጅቱ መሰረታዊ አቋምና መርህ ነው። ስለዚህ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የህወሓት ዓላማና ግብ የራሱን የበላይነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው።

በህወሓት መሪነት የተዘረጋው መንግስታዊ መዋቅር፣ ተቋማትና የአሰራር ሂደቶች በሙሉ የራሱን የበላይነትና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ላይ መሰረት ያደረጉ ናቸው። ነገር ግን የትግራይ ህዝብ፣ የህወሓት አባላትና አመራሮች ከአጠቃላዩ የኢትዮጵያ ህዝብ፣ በሀገሪቱ ከሚንቀሳቀሱ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች አንፃር ሲታይ አናሳ (Minority) ነው። በመሆኑም እንደ ፖለቲካ ድርጅት ሆነ ማህብረሰብ የህወሓት ዓላማና ግብ ብዙሃኑን (Majority) የሀገሪቱን ህዝብና የፖለቲካ ቡድኖች ያገለለ ነው።

በዚህ መሰረት ህወሓት የራሱን የበላይነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያደርገው ነገር በሙሉ የብዙሃኑን እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚፃረር ይሆናል። ህወሓት እንደ ድርጅት የተመሰረተበትን ዓላማና ግብ ለማሳካት ጥረት ባደረገ ቁጥር የብዙሃኑን መብትና ተጠቃሚነት የሚጋፋ ተግባር ይፈፅማል። በየትኛውም የፖለቲካ ማህብረሰብ ዘንድ የሰዎች መሰረታዊ ፍላጎት በእኩል ዓይነት መታየት ነው። በመሆኑም የአንድ ወገን የበላይነት እና ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ስርዓት እና አሰራር ባለበት ሀገር ዜጎች የእኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ ያነሳሉ።

የእኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዎች በተገቢው ግዜና ቦታ ምላሽ የማያገኙ ከሆነ በስልጣን ላይ ያለው የፖለቲካ ቡድን በህዝባዊ አመጽና ተቃውሞ – በህዝባዊ አብዮት – ይወገዳል። ሆኖም ግን እንደ ህወሓት ያለ የአንድ ወገን የበላይነትና ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ዓላማና ግብ ይዞ ለሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ቡድን ከብዙሃኑ የህብረተሰብ ክፍል ለሚነሳው የእኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ መስጠት አይችልም። ምክንያቱም የብዙሃኑ እኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ ምላሽ ሊያገኝ የሚችለው የአንድ ወገን የበላይነት እና ተጠቃሚነትን ማስወገድ ሲቻል ብቻ ነው።

በዚህ መሰረት ህወሓት ከብዙሃኑ የህብረተሰብ ክፍል ለሚነሳበት የእኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ ምላሽ መስጠት የሚችለው መሰረታዊ ዓላማና ግቡን በመቀየር ወይም ራሱን በራሱ በማጥፋት ነው። በሌላ በኩል ብዙሃኑ የህብረተሰብ ክፍል ለህወሓት አስተዳደር ተገዢ የሚሆነው ፖለቲካዊ ጭቆና እና ኢኮኖሚያዊ ብዝበዛን አምኖና ተቀብሎ ለመኖር ከወሰነ ብቻ ነው። ብዙሃኑ የህብረተሰብ ክፍል ጭቆና እና ብዝበዛን የሚቃወም ከሆነ ግን እንደ ህወሓት ካለ የፖለቲካ ቡድን ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግጭት ውስጥ ይገባል። በመጨረሻ ከሁለቱ አንዱ አሸናፊ ሆኖ ይወጣል።

ህዝባዊ ንቅናቄው ካሸነፈ፤ የብዙሃኑ እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ይረጋገጣል። በአንፃሩ የአንድ ወገን የበላይነትና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ላይ የተመሰረተው ስርዓት ይወድቃል። ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ሦስት አመታት በታየው ህዝባዊ ንቅናቄ አማካኝነት በህወሓት የበላይነት እና ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተው ስርዓት ወድቋል። በመሆኑም የብዙሃኑ እኩልነት ለህወሓቶች ውድቀት ነው። የብዙሃኑ ፍትህ እና ተጠቃሚነት ለህወሓቶች ፍርድና ተጠያቂነት ይዞ ይመጣል። በብዙሃኑ የህብረተሰብ ክፍል ዘንድ ድጋፍና ተቀባይነት ያገኘው ለውጥ የህወሓት አባላትና ደጋፊዎች በተቃውሞ ያጣጥሉታል። የብዙሃኑን መብትና ነፃነት ያረጋገጠው ለውጥ በህወሓቶች ዘንድ የመገፋትና ፍርሃት ስሜት ይፈጥራል። አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ስለ ሰላምና ልማት በሚዘምርበት ወቅት ህወሓቶች ግጭትና ጦርነት ለማስነሳት ጥረት ያደርጋሉ።

Friday, November 9, 2018

TPLF is responsible for sporadic clashes in different areas.



Indeed, the apartheid system was ruined by popular violence and opposition. But after the fall of the apartheid system, the damage that it causes to the total devastation is worse than worse than it was when it was in power. In this context, the last years of the anti-apartheid struggle in South Africa have clearly helped to explain the current situation in Ethiopia. But first, let's look at the similarities and trends of the anti-apartheid struggle in South Africa and Ethiopia.

Apartheid divides the South Africans into four colors: seeds, black and tan, white, black, Indian and colored. However, the anti-apartheid struggle was primarily between blacks and whites. The essence of the apartheid system is to ensure political control of a small number of the poorest people in the country. For this reason, 70% of the blacks in the country must be divided into ethnic and racial groups.
Accordingly, the apartheid division of South Africa divided the black nation, tribe and nation into ten subdivisions. Each region has its own authority to govern itself. However, it was unlawful for a region's individual to interfere in the affairs of the other region. This South African blackouts are aimed at preventing joint agenda and coordination in the national affairs.
The apartheid system is a system of dividing people who are the most important ethnic group to ensure the supremacy of power. Now the political system in Ethiopia is exactly the same in South Africa. The Tigrayan majority is based on the separation of the majority of the Amhara and Oromo peoples from the majority of the country.
Furthermore, As early as 1984 apart from the differences between South Africa's black-and-white colonies, the actions of the apartheid government show a similarity between the cause of political crisis and instability in our country and the similarities between the two systems.
There In the year of 1984, high rebellion and opposition in South Africa arose. As it has been in many parts of our country since 2008, In the year of 1986, rebellion and opposition in South Africa were raging. In both cases, government action was one and the same. Efforts have been made to hinder the demand for freedom and liberty of the people. Following this, opposition protests led to turbulence and turmoil. After this, South Africa's "Pieter Willem Botha" leader of apartheid in South Africa repeatedly promised that, like Hailemariam Desalegn, he would intensify his efforts to respond to his people's demands.
But apartheid white South Africans and the Uncle Eddie of the TPLF regime in Ethiopia were unable to bring about. Instead, they tried to force the question of freedom and liberty of the people. However, the actions of the two governments further aggravated the wrath and wrath of the people. For this reason, In 1986 in South Africa, In 2009, Ethiopia's Emergency Proclamation was proclaimed.
The apartheid system in South Africa Defense and Security officials set up the Third Force, an anti-revolutionary group. This group of militias and special police forces were designed to disrupt the Amman movement, such as Zimbabwe and Mozambique.

After the announcement, the troops were deployed to South Africa for military training and armor, dumping the anti-apartheid struggle. The apartheid system, which has been seen in the "KwaZulu Natal" region of South Africa, is exactly the same in the Somali region today.

Efforts to create an inter-ethnic conflict between various ethnic groups in South Africa are similar today with some of the Amhara, Oromia, Somali and Nile states. Therefore, it is likely that South Africa's apartheid system is trying to create an inter-ethnic conflict between the various nations and the result of the effort to sustain the rule of the white people.

In South Africa, Since 1986, the construction of a civil service to create civil conflict between different black tribes and nations. Bearing within four years, from 1990 to 1994. Certainly not a good harvest from a bitter fruit tree. Over the last four years alone, 14,000 South Africans were killed. There The number of people killed in the struggle for apartheid in 1948 was greater than those killed in the 1990 - 1994 period.

When the apartheid system in South Africa was abolished by popular violence and protests, why have 14 thousand innocent people been killed in just four years after the transitional government was established? In the first place, large numbers of South African blackbirds were killed, not by one person, but by conflict and ethnic tension between different ethnic groups. Why South Africa Blacks Are Injured After the Fallout of Apartheid? In response to this question, the former leader of the apartheid group F. W. de Klerk "and the memorandum of understanding between Nelson Mandela.

Nelson Mandela blames Genghis Khan's former generals and security forces for inciting civil-conflict conflicts between them. On the other hand, "F. Other anti-apartheid groups and leaders, including "W. de Klerk", including "²CEN, led by Nelson Mandela," claim that anti-apartheid syndicators are responsible for many years of South African blackjacking of state security forces and the rule of law. . The articles on the subject suggest that both parties have their own claims

Likewise, the reasons listed above are behind the conflicts and unrests in various areas of the country in recent months. First, the TPLF and security forces are trying to hinder the change by instigating violence and turmoil in different parts of the country. On the other hand, in the struggle against the TPLF, most of us have played our part in the struggle for the current system of chaos and conflict, prompting many to adhere to the rules and security of the country. Therefore, it should be necessary to tackle the activities of former Tale of Gen. and security officers in order to address the problem. In the same way, we have to work for the justice of the youth of our country and to cooperate with the security forces. We are all blamed for security problems in different parts of the country. So, as soon as possible, we need to unite to solve the problem.

Wednesday, October 3, 2018

Why Ethiopia hates it people

The world is full of variations. From our skin color, our desires, attitudes, and identities are completely different. There are, of course, some people who have different sexual orientation in the middle. It does not matter, then, that we must leave these inequalities aside, and we must all be the same. If we differentiate between ourselves and not, we should not say that if we do not condemn others and we do not. We must not forget that people have the unlimited right to be self-serving. They have the freedom to live in harmony with their own lives unless they touch us unless we touch them. It is impossible to override the liberties of individuals, even if this is the case of the common people. By the way, we can not just be a monopoly on the whole, people / societies may be unthankful.

In my opinion  Choosing of my  sexual orientation is  individual's privacy and it is  personal freedom. I do not believe that the government or the society should have the power to decide on this issue.

Democracy is not easy. Democracy refers to the protection of minorities from pluralism and the preservation and protection of their interests and interests. Freedom also includes the right to self-determination.

By the way, it should be noted that the same sex has existed since ancient times and has been struggling for centuries. The fact that the Bible is mentioned even extends to the extent of the affair with the children of men. It is also inappropriate to consider the issue as something new today. Misleading an existing political uprising and denouncing a political plot from the West is also wrong. But we must also remember that this same sex relationship has been recognized in the Western world today. This can be understood by turning a page into history. For example, in ancient Greek and Roman times, same-sex sexual relations were considered normal, normal and healthy.

የምጣዱ እያለ የእንቅቡን፤ የእርስ በርስ ግጭት እና የመንግስት ምላሽ

በያሬድ ሃይለማሪያም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም ግጭቶች መበራከታቸው እና መፈናቀል መቀጠሉ የአገራችንን ፖለቲካ አሳሳቢ እያደረገው እና አገሪቱንም ወደ ችግር ውስጥ እየከተታት ይመስላል። መንግስት ለችግሮቹ የሚሰ...