****ኢህአዲግ ለዋሻችሁበት ስንት ይከፍላችኋል???****
**(ለልጅ ግሩምና መሰል አለቅላቂ ባንዳዎች)***
***ስለአንድነት ፓርቲ የማውራት የሞራል ልእልናው የላችሁም!!!******
**************************************
ውድ ጓደኝቼ፡- ኢህአዲግ እንደመንግስት አያስብም፤ ሊያስብም አይችልም፤ ማሰቢያም የለውምም፤…….. አዎ! አንድ ሀገርን እመራለሁ ከሚል መንግስት፤ የማይጠበቅ ተራና የወረደ ተግባር የሚፈፅምን መንግስት ታዲያ ምን ይሉታል፡፡……………… ‹‹እሽ አይበሉኝ የሹም ዶሮ›› ፤ እንደተባለው፤ ኢህአዲግም እኔን የነካ (በስልጣኔ የመጣ፤ አይኑን ላፈር) ብሎ፤ ባገኘውና በተመቸው ሁኔታ የአንድ ትልቅ የማፊያ ድርጅት ተግባር ይፈፅማል፡፡ ……እጅግ ሲወርድ ደግሞ የህፃን ‹‹እቃ እቃ›› አይነት ጨዋታ ሲጫወት ይታያል፡፡
ኢህአዲግ በሀገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዳይኖሩ፤ተስፋ እንዲቆርጡ፤እርስ በርስ እንዲጋጩ ……….ለማድረግ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡ …….ከነዚህ መካከል ማሰር፤ ማሰደት፤ መደብደብ፤ መዝረፍ፤ ተቃዋሚዎችን በሆድ አደር ሰርጎ ገቦቹ መፈረካከስ …………. የመሳሰሉት ዋናዋናዎች ማፊያዊ ተግባራቶቹ ናቸው፡፡ ከነዚህ የፍርሀትና የስጋት ተግባራቶቹ መካከል በየመህበራዊ ድህረ-ገፁ አሰልጥኖ ባሰማራቸው ሀገር በቀል ባንዳዎቹ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እርስ በርስ ለማጋጨት፤ ተስፋ ለማስቆረጥ፤…………. ፓርቲዎቹ በህዝብ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት ለማሳጣት………ወተዘ…..በሬ ወለደ አይነት አሳሳች ዘገባዎችን ሲፅፉ፤ ሲያቦኩ፤..ሲጋግሩ ማየቱ የተለመደ ነው፡፡ አዎ! የባንዳ ተግባር ከዚህ ውጭ ሊሆን ከቶም አይችልም፡፡
የነዚህ ባንዳ ሆድ አደሮች ኢላማ ከሆኑት ፓርቲዎች በዋናነት የሚጠቀሱት የአንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡……….. እነዚህ ፓርቲዎች በአሁኑ ሰዓት ለገዢው ፓርቲ ፈተና የሆኑና እየደረሰባቸው ያለውን መንግስታዊ የማፊያ ተግባር ተቋ ቁመው፤ መከፈል ያለበትን መስዋትነት እየከፈሉ የህዝቡን ድምፅ በማስተጋባት ላይ ያሉ የህዝብ ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ……… ታዲያ እነዚህን የህዝብ ድምፆች እርስ በርስ ለማጋጨትና የትግል ጉዟቸውን ለማዳከም ከእስር፤ግርፋት እና ሌሎች አንባገነናዊ ተግባራት ጎን ለጎን በየማህበራዊ ድህረ-ገፁ መንግስት አሰልጥኖ ያሰማራቸው በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ልጅ ግሩምን የመሳሰሉ የልጅ ተግባር የሚፈፅሙ ያልበሰሉ ፌስቡከሮች ዋናዎች ናቸው፡፡ …… እነዚህ የፌስቡክ ነገረኞች በየመንደሩም ባልን ከሚስት፤ ጎረቤትን ከጎረቤት…..የማጋጨትና ፖለቲካዊ ትርፍ ለአለቆቻቸው ለማስገኘት የሚሰሩ ከሀዲ የናት ጡት ነካሾች ናቸው፡፡ ………..
ትናነት ልጅ ግሩም የተባለ በኮሜንትና በፖስት ደመወዙ በፔሮል የሚከፈለው ባንዳ ‹‹አንድነት ፓርቲ ከኢህአዲግ ጋር አብሮ ለመስራት ተስማማ›› ‹‹ አንድነት ፓርቲ ሰማያዊ ፓርቲን ከኢህአዲግ ጋር ሆኖ ለማስደብደብ ……. ይሰራል›› የመሳሰሉ፤ የልጅ ተረት ተረት ሲፅፍ አይቼ በጣም አዘንኩለት፤……ነገር ግን ‹‹ልጅ›› በመሆኑ የልጅ ስራ እየሰራ መሆኑ ሲታወቀኝ ደግሞ እንዲማርበት እንዲህ ልለው ወደድኩ፡-
‹‹ልጅ ግሩም ሆይ! ኢህአዲግ ሆድ እንጅ ጭንቅላት ያልታደለ (የማያስብ)፤ ከጥበብ ይልቅ በሀይል የሚያምን፤ ከሰላም ይልቅ ጦርነትን የሚናፍቅ፤…….ከአንድነት ይልቅ በልዩነት (በመከፋፈል) የሚያምን፤…… ከአንድ ብርጌድ ጦር አንድ ብእረኛ የሚፈራ፤ ……. የህፃን ልጅ ጩኸት የሚያስደነብረው……………. መንግስት መሆኑን በተግባር እያሳየ መሆኑን ህዝቡም፤ አንድነቶችም፤ ሰማያዊዎችም…………ሁሉም የሚያውቀው እውነታ በመሆኑ፤ እንዲሁም ህዝብም ሆነ ፓርቲዎች የወያኔን ማፊያዊ ድርጊት 23 ዓመት ሙሉ የተረዳው በመሆኑ፤ እባክህ በአንድ ፖስት፤ በኮሜንት…….. ወዘተ ታስቦ ከሚከፈላችሁ/ልህ በህዝብ እንባ የተለወሰ ገንዘብ ተዝቆ የማያልቀው የህዝብ ፍቅር ይሻላችኋልና፤…….. ወደእውነት ትመለሱና በቅድሚያ ከህሊናችሁ ታረቁ ከህዝብ ጋር ወግኑ፤……. በቃ! ይኸው ነው፤…….. ባንዳዎች እንኳንስ ስለአንድነት ፓርቲ የመተቸት ይቅርና የማሰብ እንኳ የሞራል ልእልና የላችሁም፤ ሰሚ ጆሮንም አታገኙም፡፡………….. እናም በየመንደሩ፤ በየድህረ ገፁ በየአረቄ ቤቱ እየሄዳችሁ ……….. በሬ ወለደ የማጋጨት ተግባራችሁን እዚሁ ላይ አቁሙ እላለሁ፡፡›› ………….. እመነኝ ኢህአዲግ በሰላማዊ ታጋዮቻችን ቆራጥ ተጋድሎ፤ ይወድቃልልልልልል…………!!!!! ……ሆድ አደር ተላላኪ ግን ዳር ትቀሪያለሽ………!!!! …….. ስለዚህ………..!!!!....... ድል የህዝብ ነው!!!
No comments:
Post a Comment